መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ 21-2012-በኒውዝላንድ የሽብር ጥቃት የፈጸመው ግለሰብ የእድሜ ልክ እስር ያለ ምህረት በሚል ተፈረደበት፤ፍርዱ በኒዉዝላንድ ታሪክ የመጀመሪያው ነዉ

በኒዉዝላንድ ክራይስት ቸርች ከተማ 51 ሰዎች በተገደሉበት የመስጊድ የሽብር ጥቃት ያደረሰዉ ግለሰብ በኒዉዝላንድ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የእድሜ ልክ እስር ያለ ምህረት ተላልፎበታል፡፡የ29 ዓመቱ ብሪተን ታራንት በፈጸመው የሽብር ድርጊት ከተገደሉት 51 ሰዎች በተጨማሪ 40 ሰዎች ክፉኛ ቆስለዋል፡፡
ጉዳዩን የተከታተለዉ የኒዉዝላንድ ፍርድ ቤት ድርጊቱን ምህረት የለሽ ከሰብዓዊነት ዉጪ የተፈጸመ ሲል ገልጾታል፡፡በኒዉዝላንድ ታሪክ የመጀመሪያዉ ያስባለዉ በእስር እድሜ ልክ እንዲቀጣ ከማድረግ ባለፈ በሞት ይህንን ምድር እስካልተሰናበተ ድረስ ከእስር አይለቀቅም፡፡
በኒዉዝላንድ የፍትህ ስርዓት ዉስጥ የሞት ቅጣት ተግባራዊ አይደረግም፡፡የ29 ዓመቱ የነጭ የበላይነት አቀንቃኝ ታራንት በተመለከተ የአዉስትራሊያ ጠቅላይ ሚንስትር ሞሪሰን የቀኝ ዘመም ጽንፈኛ ሰዉ ነዉ ሲሉት ገልጻዋል፡፡
ታራንታ በአዉስትራሊያ ኒዉ ሳዉዝ ዌልስ የተወለደ ሲሆን ወላጅ አባቱ የጽዳት ባለሙያ ወላጁ እናቱ ደግሞ መመህር ነበሩ፡፡ወላጅ አባቱ በ2010 ህይወቱ ማለፉን ተከትሎ አዉስትራሊያን በመልቀቅ በእስያና አዉሮጳ መዘዋወር ችሏል፡፡
በጉዞዉ ወቅት ምናልባትም አእምሮንም የሚቀይር ነገር ሳይፈጠር እንዳልቀረ አያቱ ተናግረዋል፡፡ወደ ኒዉዝላንድ በ2017 ያቀና ሲሆን ጥቃቱን ከመፈጸሙ በፊት ባለ 74 ገጽ ጹሁፊ በኢንተርኔት ላይ ማስፈሩ ይታወሳል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *