መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ 21-2012-የብስራት ማለዳ አጫጭር ዓለም አቀፍ መረጃዎች

~ የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በአይቮሪኮስት ምርጫ ፕሬዝዳንት ኦታሬ ለሶስተኛ ዙር በድጋሚ እወዳደራለዉ ማለታቸዉን ተከትሎ ሀገራቸዉ ጣልቃ እንድምትገባ አስታወቁ፡፡ፕሬዝዳንት ኦታሬ ህገመንግስቱን በሚጣረስ መልኩ በቀጣዩ ምርጫ ለመሳተፍ እየተዘጋጁ ይገኛል፡፡
~ በግብጽ መዲና ካይሮ ቅንጡ ሆቴል በሆነዉ ፌርሞንት ናይል ሲቲ አደንዛዥ እጽ በመጠቀም ዘጠኝ በመሆን አንዲት ሴትን አስገድደዉ የደፈሩ ተጠርጣሪዎች ግብጽን ለቀዉ መዉጣታቸዉን የሀገሪቱ ጠቅላይ አቃቢ ህግ አስታዉቋል፡፡ተጠርጣሪዎቹ ድርጊቱን ከስድስት ዓመት በፊት ፈጽመዋል፡፡
~ ዩኒሴፍ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የተነሳ ትምህርት በኦንላይንድ መሰጠት ቢቀጥልም 463 ሚሊየን የአለም ህጻነት ከአገልግሎቱ ተገለዋል ሲል አስታወቀ፡፡ዋንኛ ተጎጂ የሆኑት የአፍሪካ፣የፓስፊክና የደቡብና ምስራቃዊ እስያ ሀገራት ተማሪዎች ናቸዉ፡፡
~ የደቡብ ኮርያ ገዢዉን ፓርቲ ስብሳባ ሲዘግብ የነበረ የፎቶ ጋዜጠኛ በኮሮና ቫይረስ መጠቃቱን ተከትሎ የሀገሪቱ የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ተዘግቶ እንዲቆይ አባላቱም ራሳቸዉን እንዲያገሉ ዉሳኔ ተላልፏል፡፡
~ ኤር ኒዉዝላንድ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የተነሳ የ300 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ኪሳራ እንዳጋጠመዉ አስታወቀ፡፡1/3ኛዉን ወይም 12,500 ሰራተኞቹን ሊቀንስ እንደሚችል አስታዉቋል፡፡
~ በደቡብ ቻይና ባህር የይገባኛል ዉዝግብን 8 ሀገራት የሚያነሱ ቢሆንም ቻይና ሀይል በመጠቀም አካባቢዎን መቆጣጠር ቀጥላለች በሚል አሜሪካ በ24 የቻይና ኩባንያዎች ላይ ማዕቀብን ጣለች፡፡
~ የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ማይክ ፔንስ በቀጣዩ የሀገሪቱ ምርጫ ባይደን ካሸነፉ አሜሪካ ያልተረጋጋች ሀገር ትሆናለ ሲሉ ተናገሩ፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *