መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ 22-2012-በኤፍ ቢ አይ(FBI) ተፈላጊ ከተባሉ አስር ወንጀለኞች መካከል አንዱ በቁጥጥር ስር ዋለ

ሁለት ሴት ልጆቹን በመግደል ወንጅል በኤፍ ቢ አይ ለ12 ዓመታት ሲፈለግ የነበረዉ ያሲር አብደል ሰኢድ በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡እ.ኤ.አ በ2008 ዓመት ሁለት ሴት ልጆቹን ሳራ ያሲር እና አሚና ያሲርን ተኩሶ ገድሏል፡፡
ኤፍ ቢ አይ በግብጽ እንደተወለደ የሚነገርለትን እና ሁለት ሴት ልጆቹን ተኩሶ የገደለዉን አባት ከፍተኛ ተፈላጊ ወንጀለኛ በማለት በቁጥጥር ስር ለማዋል ከፍተኛ ዘመቻ ከፍቶ ቆይቷል፡፡
ግለሰቡ ከአስር ተፈላጊ ወንጀለኞች ዝርዝር ከስድስር ዓመታት በፊት መካተቱ ይታወሳል፡፡የሟቾቹ ወላጅ እናት ኦዌንስ ገዳዩ አባታቸዉ በቁጥጥር ስር በመዋሉ የልጆቼ ነፍስ አሁን በሰላም ታርፋለች ስትል ተናግራለች፡፡
በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *