መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ 25፣2012-በህንድ በአንድ ቀን ውስጥ ብቻ ከ 78ሺ በላይ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መጠቃታቸው ተሰማ

በ24 ሰዓት ውስጥ 78‚761 ሰዎች በህንድ በኮሮና ቫይረስ መጠቃታቸውን ተከትሎ በ24 ሰዓት ውስጥ የተመዘገበ የዓለም ከፍተኛው ስለመሆኑ ታውቋል፡፡
በህንድ ኢኮኖሚውን ለመታደግ በሚል ተጥሎ የነበረውን እንቅስቃሴን የሚከለክል ህግ እንዲነሳ መደረጉ ይታወሳል፡፡
የካርዲዮሎጂ ዶክተር ማንኦጂ ኩማር እንደተናገሩት ወረርሽኙ በገጠራማ የህንድ ግዛቶች መዛመቱ በአንድ ቀን ከፍተኛ የተጠቂዎች ቁጥር እንዲጨምር ሆኗል ብለዋል፡፡
በህንድ የቫይረሱ ተጠቂዎች ቁጥር 3.6ሚሊዮን ሲደርስ ከ 64ሺ በላይ ሰዎች ሕይወት አልፏል፡፡
የጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ መረጃ እንደሚያሳየው በመላው ዓለም በኮሮና ቫይረስ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 25ሚሊየን ሲያልፍ ከነዚህ መካከል 17 ሚሊዮን ሰዎች አገግመዋል፡፡ የ850 ሺህ ሰዎች ህልፈትም ሪፖርት ተደርጓል፡፡
በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *