መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ 26፣2012-የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በናይጄሪያ የፊልም ኢንዱስትሪ ዉስጥ መልካም እድል ይዞ መምጣቱ ተሰማ

በሰሜናዊ ናይጄሪያ የሙስሊም ማህበረሰብ መኖሪያ በሆኑ ግዛቶች የፊልም ኢንዱስትሪዉ እያደገ ይገኛል፡፡ካኖ የተባለችዉን ከተማ መነሻ በማድረግ የሚሰሩ ፊልሞች ካኒዉድ የሚል ስያሜን እያገኙ መጥተዋል፡፡

በካኒዉድ 502 የፊልም ፕሮዳክሽኖች ያሉ ሲሆን ከ30ሺ በላይ ሰዎችን በመቅጠር መሰረተ ሰፊ ሆኗል፡፡ኖርዝፍሊክስ በተባለ አሰራር ባለሙያዎችን በኢንተርኔት ገቢ ተጠቃሚ የሚያደርግ አሰራር ተዘርግቷል፡፡

በኮሮና ወረርሽኝ ዘመን በኢንተርኔት ከተመልካች የሚገኘዉ ገቢ መጨመር ባለሙያዎችን የሚያግዝ ሆኗል፡፡

በናይጄሪያ የፊልም ኢንዱስትሪ ዉስጥ ካኒዉድና ኖሊዉድ በሚል በሁለት የሚከፈሉ ሲሆን ኖሊዉድ ከተመሰረተ ከሶስት ዓመታት በኃላ ካኒዉድ ተመስርቷል፡፡

በካኒዉድ የሚቀርቡ ፊልሞች ከእስላማዊ ትዕዛዛት ያፈነገጡ አይደሉም፡፡በሳምንት በናይጄሪያ በአማካይ ከ70 ያላነሱ ፊልሞች ለእይታ ይበቃሉ፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *