መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ 26፣2012-የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በሊባኖስ አዲስ የመንግስት ካቢኔ እንዲመሰረት ጥሪ አቀረቡ

ከህዝብ እንደራሴዎች ከፍተኛዉን ይሁንታ በማግኘት በጀርመን የሊባኖስ አምባሳደር የነበሩት መስጠፋ አዲብ አዲሱ የሊባኖስ ጠቅላይ ሚንስትር ተብለዋል፡፡ኢማኑኤል ማክሮን ለመንግስት ምስረታ ከፍተኛ ድጋፍ ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡

በቤሩት ያጋጠመዉን ፍንዳታ ተከትሎ የሊባኖስ መንግስት ስልጣን መልቀቁ የሚታወስ ሲሆን የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ከፍንዳታዉ ወዲህ ለሁለተኛ ጊዜ በትላንትናዉ እለት ወደ ቤሩት አቅንተዋል፡፡

ማክሮን ለሊባኖስ ፖለቲከኞች ሙስናን እንዲዋጉ፣የፋይናንስ ብክነትን እንዲያስቀሩ ግፊት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ወደ ስልጣን የመጡት አዲብ በአስቸጋሪ የሊባኖስ ጊዜ ላይ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ሀላፊነት በጎደለዉ መልኩ የተከማቸዉ አሙኒየም ናይትሬት ባስከተለዉ ፍንዳታ ከ200 በላይ ሰዎችን ህይወት ሲነጥቅ፣በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ለአካል ጉዳት ዳርጓል፡፡በርካታ የመኖሪያ ቤቶችም ወደ ፍርስራሽነት ተቀይረዋል፡፡

የ48 ዓመቱ አዲሱ የሊባኖስ ጠቅላይ ሚንስትር አዲብ በሊባኖስና ፈረንሳይ የህግና የፖለቲካል ሳይንስ ትምህርታቸዉን ተከታትለዋል፡፡ባለፉት ሰባት ዓመታት በጀርመን የሊባኖስ አምባሳደር ነበሩ፡፡

በሚኪያስ ጸጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *