መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ 28፤2012-አሜሪካ ለአለም የጤና ድርጅት የምታደርገውን የገንዘብ ድጋፍ እንደምታቋርጥ አስታወቀች።

የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር በአለም የጤና ድርጅት ውስጥ የአባልነት 62 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ክፍያን እንደማይፋፅም ይፋ አድርጓል።
ይህ ውሳኔ የተላለፈው አሜሪካ ኮቫኤክስ ከተሰኘው አለም አቀፍ የኮሮና ቫይረስ ክትባት ምርምርና ስርጭት ራሷን ማግለሏን ካስታወቀች በኃላ ነው።
አሜሪካ ከአለም የጤና ድርጅት አባልነት ይፋዊ በሆነ መልኩ ለመውጣት አንድ አመት ጊዜን የሚጠይቅ ሲሆን እስከዛው ግዴታዎቿን መወጣት ይኖርባታል።
አሜሪካ በተመረጡ መርሃ ግብሮች ላይ ብቻ አስተዋጾ እንደምታደርግ አስታውቃለች።አሜሪካ ለድርጅቱ ከምታዋጣው ዓመታዊ 120 ሚሊየን ዶላር ውስጥ አስቀድማ 52 ሚሊየን ዶላር ከፍላለች።


በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *