መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ 28፤2012-ኬንያ አልሻባብን ሲደግፉ ነበሩ ያለቻቸውን ግለሰቦች ንብረት እንዳይንቀሳቀስ አገደች

በሶማሊያ የሚንቀሳቀሰውን የጂሃዲስት ቡድን የገንዘብ ድጋፍ ያደርጋሉ ያላቸውን ዘጠኝ ግለሰቦች ንብረት እንዳይንቀሳቀስ ኬንያ እገዳ አድርጋለች።
የኬንያ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚንስቴር እንዳስታወቀው እርምጃው በሀገር ውስጥ ያሉ የሽብር ቡድኖች እንቅስቃሴን ለመከላከል ያግዛል ሲል ይፋ አድርጓል።
ዘጠኙ ግለሰቦች የኬንያ ዜግነት እንዳላቸው ተነግሯል።የኬንያው ፕሬዝዳንት ኧሁሩ ኬንያታ እንደተናገሩት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መስፋፋት ሽብርተኝነት ስር እንዲሰድ መሰረት ሊሆን ስለሚችል በትኩረት መስራት ተገቢ ነው ብለዋል።
አልሻባብ እ.ኤ.አ ከ2011 አንስቶ ተደጋጋሚ ጥቃትን በኬንያ እየሰነዘረ ይገኛል።ለዚህም መነሻው የኬንያ ጦር ወደ ሶማሊያ እጁን በማስገባቱ ቡድኑን ለመደምሰስ በመዋጋቱ የተነሳ ነው።
በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *