መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ ነሐሴ 28፤2012-የብስራት ማለዳ አጫጭር ዓለም አቀፍ መረጃዎች።

~ አሜሪካዊው ተናዋናይ ዱዌን ጆንሰን(ዚ ሮክ) እርሱና ባለቤቱ እንዲሁም ሁለት ሴት ልጆቹ በኮሮና ቫይረስ ከሁለት ሳምንት በፊት መጠቃታቸው ተሰማ።በአመቱ ዱዌን 87.5 ሚሊየን ዶላር በመሰብሰብ ቁጥር አንድ ተዋናይ መባሉ ይታወሳል።
~ የህንዱ ጠቅላይ ሚንስትር ናሬንድራ ሞዲ የቲውተር አካውንት በበይነ መረብ ጠላፊዎች መጠለፉ ተሰማ።.ገጹ 61 ሚሊየን ተከታዮች አሉት።ቲውተር በበኩሉ የተጠለፈውን አካውንት ደህንነት አረጋግጫለው ብሏል።
~ በአሜሪካ የዲሞክራት የፕሬዝዳንት እጩ ጆ ባይደን ሁለት ጥቁር አሜሪካውያን ላይ የተኮሱ የፖሊስ አባላት ተጠያቂ እንዲሆኑ ጥሪ አቀረቡ።ብሌክ የተባለው ጥቁር አሜሪካዊ 7 ጊዜ ተተኩሶበት በከፋ የጤና ሁኔታ ውስጥ ይገኛል።ታይለር የተባለች ሌላ ሴት በፖሊስ የተተኮሰባት ሲሆን ሁኔታው ቁጣን ቀስቅሷል።
~ እውቁ የሩሲያ የተቃዋሚ ፖለቲከኛ አሌክሲ ናቫሊን ነርቭን በሚጎዳ ኬሚካል መመረዙን ጀርመን አስታወቀች።ናቫሊን ፑቲን ስልጣን ማራዘመቸውንና በፀረ ሙስና ትግሉ ታዋቂ ነው።በእንግሊዝ ነዋሪ የሆነው የቀድሞ የሩሲያ ሰላይ ሰርጌ ስክሪፓል በኬሚካል መመረዙ ይታወሳል።ከዚህ ድርጊት ጀርባ ሩሲያ መወንጀሏ አይዘነጋም
~ በህንድ በ24 ሰዓት ውስጥ ብቻ 83,883 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መጠቃታቸው ተሰማ። በመላዉ አለም በአንድ ቀን ውስጥ ከፍተኛ ተጠቂዎች ተብሏል።በህንድ የሟቾች ቁጥር 67,376 ደርሷል።
~ አለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት አሜሪካን ትኩረት አድርጓል በሚል የዋሽንግተን አስተዳደር በፍርድቤቱ ባለስልጣናት ላይ ማዕቀብ ጣለ።ማዕቀቡን ፍርድ ቤቱ አውግዟል።
~ የቀድሞ የጣልያን ጠቅላይ ሚንስትር ሲልቪዮ በርልስኮኒ የኮሮና ቫይረስ ህክምና እያደረጉ መሆናቸው ተሰማ።
በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *