መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ 28፤2012 -ኢን ኤንድ አውት በርገር ስያሜውን መቀየሩን አስታወቀ።

በአዲስ አበባ ከሚገኙ የፈጣን ምግብ አቅራቢዎች መካከል አንዱ የሆነው ኢን ኤንድ አውት በርገር ስሙን ወደ ኢን ጆይ በርገር መቀየሩን በዛሬው እለት ጋዜጠኞችን በመጥራት አስታውቋል፡፡
ድርጅቱ ስያሜውን ለመቀየር ከሀገር ውስጥ ባሻገር በዓለም አቀፍ ደረጃ ቅርንጫፎችን ለመክፈት በተደረገው ጥረት ሌላ በኢን ኤንድ አውት ስም የተመዘገበ ተቋም በመኖሩ የተነሳ እና ከሚሰጡው አገልግሎት ጋር ትርጉም ያለው ስያሜ ለመስጠት ታስቦ እንደሆነ የድርጅቱ ባለቤት እና ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ሳለአምላክ አንዳርጌ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡
ከአስር አመት በፊት ሲመሰረት በ200ሺ ብር ካፒታል የተቋቋመው የአሁነኑ ኢን ጆይ በርገር ካፒታሉን ወደ 200 ሚሊየን ብር ማድረስ ችሏል።
በአዲስ አበባ በሚገኙት ሰባት ቅርንጫፎቹ የሰራተኞቹን ቁጥር ከ10 ወደ 240 ቋሚ እና 60 ጊዜያዊ ሰራተኞች ከፍ ማድረግ ችሏል።
ዓለም አቀፉ የኢን ኤንድ አውት የፈጣን ምግቦች አቅራቢ ተቋም እ.ኤ.አ በ1948 በአሜሪካ ካሊፎርኒያ ተመስርቷል።

ትግስት ላቀው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *