መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ 29፤2012-የብስራት ማለዳ አጫጭር ዓለም አቀፍ መረጃዎች


~ የባትማን ፊልም ቀረጻ መቋረጡ ይፋ ተደረገ፡፡ለዚህ መነሻዉ በፊልሙ ላይ የሚተዉነዉ እንግሊዛዊዉ ተዋናይ ሮበርት ፓቲሰን በኮሮና ቫይረስ መጠቃቱን መረጋገጡን ተከትሎ ነዉ፡፡
~በብራዚል በኮሮና ቫይረስ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር ከ4 ሚሊየን በላይ ሆነ፡፡በብራዚል የቫይረሱ ተጠቂዎች ቁጥር በከፍተኛ ፍጥነት እየጨመረ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 125,000 ደርሷል፡፡
~ በህንድ በ24 ሰዓት ዉስጥ 83,341 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መጠቃታቸዉ ተሰማ፡፡አጠቃላይ የቫይረሱ ተጠቂዎች በመላዉ ህንድ 3.94 ሚሊየን ሲደርስ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 68,472. ስለመድረሱ ሪፖርት ተደርጓል፡፡
~ በጃማይካ በተደረገዉ ምርጫ ገዢዉ ፓርቲ በድጋሚ ማሸነፉ ተሰማ፡፡ከምክር ቤቱ መቀመጣ ከ63 ወንበር 49ኙን በጠቅላይ ሚንስትር አንድሪዉ ሆልነስ የሚመራዉ ሌበር ፓርቲ አሸናፊ ሆኗል፡፡
~ በሩዋንዳ መዲና ኪጋሊ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛን በማያደርጉና በአግባቡ በማይጠቀሙ ሰዎች ላይ መንግስት በ10 የአሜሪካን ዶላር መቀጮ መቅጣት እንደሚጀምር አስታወቀ፡፡
~ የአይኤስ የሽብር ቡድን የዲጂታል ቤተ መጽሃፍት ማግኘቱን ስትራቴጂን ዲያሎግ የተባለ ኢንስቲትዮት አስታወቀ፡፡ቤተ መጽሃፍቱ ከ90ሺ በላይ የፕሮፓጋንዳ ዲጂታል ጹሁፎች እንዳሉበት ተረጋግጧል፡፡
~ የአሜሪካ የዲሞክራት እጩ ጆ ባይደን በፖሊስ ሰባት ጊዜ ተተኩሶበት ከፍተኛ ጉዳት ዉስጥ ከሚገኘዉ ጥቁር አሜሪካዊ ብሌክ ጋር በስልክ መነጋገራቸዉ ተሰማ፡፡ትራምፕ በዊስኮንሲ በነበራቸዉ ጉብኝት ከብሌክ ቤተሰብ ጋር እንደማይገናኙ መናገራቸዉ አይዘነጋም፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *