መደበኛ ያልሆነ

ጷግሜ 2፤2012 – ቱርክ በሰሜናዊ ሳይፕረስ የጦር ልምምድ ማድረግ መጀመሯ ተሰማ

ቱርክ በምስራቃዊ ሜድታራኒያ ከግሪክ ጋር ያላት ውጥረት ተጠናክሮ ቢቀጥልም ይህንን የጦር ልምምድ መልዕክት ለማስተላለፍ በሚል ተጠቅማበታለች፡፡

ቱርክ እና ግሪክ የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃልኪዳን ኔቶ አባል ሀገራት ሲሆኑ በምስራቃዊ ሜድትራኒያ ባለው የተፈጥሮ ጋዝና ነዳጅ ክምችት ውዝግብ ውስጥ ይገኛል፡፡

እ.ኤ.አ በ 1974 በግሪክ የጦር መሪ የተቀነባበረ መፈንቅለ መንግስት በቱርክ ከተካሄደ በኋላ ቱርክ በሰሜናዊ ሳይፕረስ በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮችን አስፍራለች፡፡ ሳይፕረስ ደቡባዊ ክፍልን ግሪክ ተቆጣጥራዋለች፡፡

ቱርክ በሳይፕረስና በግሪክ ላይ በምታራምደው አቋም የተነሳ በተያዘው ወር በአውሮፓ ምክር ቤት ማዕቀብ ሊጣልባት እንደሚችል ፈረንሳይ አስጠንቅቃለች፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *