መደበኛ ያልሆነ

ጷግሜ 2፤2012-ኖቫክ ጆኮቪች በውድድር ላይ ዳኛዋን በድንገት በቴኒስ ኳስ በመምታቱ ከውድድሩ እንዲሰናበት ተደረገ

እውቁ የአለማችን ቁጥር አንድ የሜዳ ቴኒስ ተጫዋች ኖቫክ ጆኮቪች በአሜሪካ የሜዳ ቴኒስ ውድድር ላይ በድንገት ዳኛዋን በኳስ በመምታቱ ከውድድሩ ተሰናብቷል።

ጆኮቪች በውድድሩ ላይ 6 ለ 5 እየተመራ ነበር።ዳኛዋን በኳስ የመታት በንዴት ሳይሆን በስህተት ቢሆንም ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፍ አልቻለም።

ከዚህ በፊት በአውስትራሊያ ኦፕን 6 ሰዓት ከ15 ደቂቃ በፈጀ ውድድር ሰርባዊው ጆኮቪች ከ2 ለ 0 መመራት ተነስቶ ናዳልን 3 ለ 2 ማሸነፉ ይታወሳል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *