መደበኛ ያልሆነ

ጷግሜ 2፤2012-የብስራት ማለዳ አጫጭር አለምዓቀፍ መረጃዎች

~ በሴኔጋል መዲና ዳካር በሶስት የክረምቱ ወራት ከተመዘገበው በላይ በ24ሰዓታት ውስጥ ከፍተኛ ዝናብ ተመዘገበ፡፡ በሀገሪቱ ከፍተኛ የጎርፍ አደጋ ያስከተለ ሲሆን ፕሬዝደንቱ የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ እቅድን ይፋ አድርገዋል፡፡

~ የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የፎክስ ኒውስ ብሄራዊ የደህንነት ዘጋቢ ከስራ እንድትሰናበት ፍላጎት እንዳላቸው ተነገረ፡፡ ዘጋቢዋ ጄነፈር ግሪፍን በአሜሪካ ጦር የቀድሞ አመራሮች በፕሬዝዳንቱ ላይ ንቀት እንዳላቸው የሚያስተጋባ ዘገባ መስራቷ ትራምፕን አበሳጭቷል፡፡ ትራምፕ በቬትናም ጦርነት የአሜሪካን ተሳትፎ ማሳነሳቸው ይታወሳል፡፡

~ በፀጥታ አካላት ሰባት ጊዜ የተተኮሰበት ጥቁር አሜሪካዊ ጃኮብ ብሌክ ከሆስፒታል ባስተላለፈው መልዕክት ለመተንፈስ ይቸግረኛል ሲል ተናግሯል፡፡ ‹‹ለመኖር ግን ገና ሕይወት አለን›› ሲል አክሏል፡፡ ብሌክ በከፍተኛ ህመም ውስጥ ስለመሆኑ ተገልጿል፡፡

~ የቻይና የመድሃኒት ኩባንያ ሲኖቫክ 3ሺ ለሚሆኑ ሰራተኞቹና ቤተሰቦቻቸው የኮሮና ቫይረስ ክትባት መስጠቱ ተሰማ፡፡

~ በብራዚል ባለፉት 24ሰዓታት 447ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሕይወታቸው ማለፉ ተሰማ፡፡ በመላው ሀገሪቱ በቫይረሱ ህይወታቸውን ያጡ ዜጎች ቁጥር ከ 126 ሺ ሲልቅ የተጠቂዎቹ 4.14 ሚሊዮን ደርሷል፡፡

~ በባንግላዲሽ በአንድ መስጂድ ላይ ባጋጠመ ፍንዳታ 24 ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ፡፡ ፍንዳታው በመዲናዋ ዳሃካ ያጋጠመ ሲሆን ምክንያቱ አልተገለፀም፡፡

~ በደቡብ ኮሪያ ሀሺን የተባለ ወጀብና አውሎ ንፋስ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ይገኛል፡፡ በሰዓት 126ኪ.ሜ የደረሰ ንፋስ ተመዝግቧል፡፡ በዚህም ከ 300 በላይ በረራዎች ሲሰረዙ 5000 ሰዎች የሃይል አቅርቦት ተቋርጦባቸዋል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *