መደበኛ ያልሆነ

ጷግሜ 3፤2012-የቀድሞ የዶናልድ ትራምፕ ጠበቃ በአዲሱ መጽሃፉ ላይ ትራምፕ የወንጀለኛ ቡድንን እንደሚመራ ሰው ናቸው ሲል መጽሃፉ ተሰማ

የቀድሞ የዶናልድ ትራምፕ ጠበቃ ሚካኤል ኮኧን ዲስሎያል ኤ ሜሞር በተሰኘዉ አዲሱ መጽሃፉ ትራምፕ የወንጀለኛ ቡድን ውስጥ እንዳለ ሰዉ ዓይነት ናቸው ሲል ጽፏል፡፡ስለ ጥቁሮች ያላቸዉ ግንዛቤ አነስተኛ መሆኑን ጸሀፊዉ አብራርቷል፡፡

በትራምፕ የምረጡ ዘመቻ ወቅት ከነበረ የፈይናንስ ስርዓት ያልተከተለ እና ከሌሎች ወንጀሎች ጋር ተያይዞ ሚካኤል ኮኧን በማረሚያ ቤት ዉስጥ ሆኖ የጻፈዉ መጽሃፍ ስለመሆኑ ታዉቋል፡፡ትራምፕ ስለ ጥቁሮች ከሙዚቃ እስከ ባህል ደግሞም ፖለቲካዉን ጭምር አነስተኛ ግንዛቤ ያላቸዉ ሰዉ ናቸዉ ሲል በመጽሃፉ አብራርቷል፡፡

የደቡብ አፍሪካ የቀድሞ ፕሬዝዳንትና የጸረ አፓርታይድ ታጋይ ኔልሰን ማንዴላ መሪ አልነበሩም ሲሉ ትራምፕ መናገራቸዉን በመጽሃፉ የቀድሞ የፕሬዝዳንቱ ጠበቃ አስፍሯል፡፡በመጽሃፉ እንደተገለጸዉ ትራምፕ በአንድ ወቅት እንዲህ ሲሉ ተናግረዋል ይላል በጥቁሮች የሚመራ ሀገር አንድ ሀገር እስቲ ንገሩኝ ፤ሁሉም የተሟሉ መጸዳጃ ቤቶች ሊሆኑ ይችላል እንዲ ከዛ አያልፍም ሲሉ ትራምፕ መናገራቸዉ በመጽሃፉ ተካቷል፡፡

በሌላ ጊዜ ደግሞ ትራምፕ ስለ እስፓኒኮች ሲናገሩ ከእነርሱ የምርጫ ድምጽ አላገኝም እንደ ጥቁሮች ናቸወ እነሱ ህዝቡ አይደሉም ሞኞች ናቸዉ ሲሉ መናገራቸዉን በመጽሃፉ ሰፍሯል፡፡መጽሃፉን በተመለከተ ዋይት ሀዉስ ባወጣዉ መግለጫ በዉሸት የተሞላ ሲል ጠርቶታል፡፡በመጽሃፉ ሚካኤል ኮኧን ትራፕን ዉሸታም፣ዘረኛ፣የወንጀለኛ ቡድን አለቃ ሲል የገለጻቸዉ ሲሆን ዋይት ሀዉስ በተመሳሳይ ደራሲ ታማኝነቱን ያጣ ሰዉ ነዉ ሲል መግለጫ አዉጥቷል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *