መደበኛ ያልሆነ

ጷግሜ 3፤2012-የብስራት ማለዳ አጫጭር ዓለም አቀፋዊ መረጃዎች

~ የቀድሞ የግብጽ ፕሬዝዳንት ሞሃመድ ሙርሲ ወንድ ልጅ ህይወቱ ያለፈዉ መንግስት እንዳስታወቀዉ በልብ ህመም ሳይሆን በገዳይ ንጥረ ነገር ተመርዞ ስለመሆኑ የቤተሰቡ ጠበቃ አስታወቁ፡፡የሙርሲ የመጨረሻ ወንድ ልጅ አብዱላህ ሙርሲ በ25 ዓመቱ በጊዛ ሆስፒታል ህይወቱ ማለፉ ይታወሳል፡፡

~ በሶማሊያ በመኪና ላይ የተጠመደ ቦምብ ፈንድቶ ሶስት የሶማሊያ ልዩ ሀይል አባላት ሲገደሉ አንድ አሜሪካዊ ወታደር ክፉኛ ተጎድቷል፡፡ጥቃቱ ጃና አብዳል በተባለ አካባቢ የተፈጸመ ሲሆን አልሻብብ ሀላፊነቱን እንደሚወስድ አስታዉቋል፡፡

በካሊፎርኒያ ያጋጠመዉ ሰደድ እሳት በከፍተኛ ፍጥነት እየተስፋፋ መሆኑ ተሰማ፡፡ከ14ሺ በላይ የድንገተኛ ባለሙያዎች እሳቱን ለማጥፋት ከፍተኛ ርብርብ እያደረጉ ይገኛል፡፡

~ በቻይና እና ህንድ መካከል በተፈጠረው የተኩስ ልዉዉጥ ጸብ ጫሪ ድርጊቱን ቀድማ የጀመረችዉ ህንድ ናት ስትል ቻይና ተናገረች፡፡የህንድ ወታደሮች ህገወጥ በሆነ መልኩ የሼኖፓን ተራራማ ክፍል መሻገራቸዉ የተኩስ ልዉዉጡ እንዲፈጠር ምክንያት ሆኗል፡፡

~ ሳዑዲ መራሹ ጥምር ጦር እ.ኤ.አ ከ2015 አንስቶ በየመን መፈጸም በጀመረዉ የአየር ላይ ጥቃት 3,500 የሚሆኑ ህጻናት መገደላቸዉን የየመን የሰብዓዊ መብት ተቋም አስታወቀ፡፡

~ የሳዑዲ አረቢያ ፍርድ ቤት ከጋዜጠኛ ጀማል ካሾግጂ ግድያ ጋር በተያያዘ እጃቸዉ አለበት ያላቸዉን ስምንት ሰዎች ከሰባት እስከ ሀያ አመታት በእስር መቅጣቱ ተሰማ፡፡ጋዜጠኛዉ በቱርክ ኢስታንቡል በሚገኘዉ የሳዑዲ ቆንስላ ጽህፈት ቤት ዉስጥ የተገደለ ሲሆን አስክሬኑ አለመገኘቱ ይታወሳል፡፡

~ የጃፓን የመንግስት ካቢኔ ዋና ጸሀፊ ዮሺሃይድ ሱጋ ቀጣዩ የጃፓን ጠቅላይ ሚንስትር እንደሚሆኑ ከፍተኛ ግምት እየተሰጣቸዉ ይገኛል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *