መደበኛ ያልሆነ

ጷግሜ 4፤2012-ኔልሰን ማንዴላን በተመለከተ ዶናልድ ትራምፕ ተናገሩ በተባለው መረጃ ዙሪያ የደቡብ አፍሪካ ገዢው ፓርቲ ከፋፋይ ሰው ናቸው ሲል መናገሩ ተሰማ

የደቡብ አፍሪካ ገዢው ፓርቲ አፍሪካ ናሽናል ኮንግረስ የቀድሞ የዶናልድ ትራምፕ ጠበቃ ሚካኤል ኮፕን በአዲሱ መፅሃፉ ትራምፕ ስለ ማንዴላ የተናገሩትን አስፍሯል፡፡ ሚካኤል ኮፕን Disloyal A Memoir በተሰኘው መፅሃፍ ትራምፕ ስለ ማንዴላ ሲናገሩ እርሱ መሪ አይደለም ብለዋል ሲል ጽፏል፡፡ ጥቁር ሁኖ ሃገር የሚመራ ሰው እንዳለ ከነገራችሁ ከተሟላ መጸዳጃ ቤት ያለፉ አይደለም ሲሉ ትራምፕ ተናግረዋል ሲል የቀድሞ ጠበቃቸው ፅፏል፡፡ ይህንኑ ተከትሎ የደቡብ አፍሪካ ገዢው ፓርቲ አፍሪካ ናሽናል ኮንግረስ ማንዴላ ለ 27ዓመታት የታሰረው ለዜጎች መብት መከበር ነው፡፡ ዲሞክራሲ እንዲከበር የሰራ ሰው ነው፡፡ ትራምፕ ግን ከፋፋይ ፣ የተሳሳተ ሃሳብ ያላቸው እና አክብሮት የጎደለው ሰው ነው ሲሉ ፓርቲው ትራምፕን ወቅሷል፡፡

በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *