መደበኛ ያልሆነ

ጷግሜ 4፤2012-አሜሪካ ከቻይና ሺጂአንግ ግዛት ተመርተው የሚመጡ ምርቶች ወደ ሃገሬ እንዳይመጡ ስትል

ከለከለች ሀገሪቱ ከዚህ ውሳኔ የደረሰችው በግዳጅ የሰራተኞችን በመበዝበዝ የሚመረቱ ናቸው ስትል ነው፡፡ የትራምፕ አስተዳደር በቻይና ሺጂአንግ ግዛት በሚገኙ ሙስሊሞች ላይ የሚደርሰውን ጫና እያወገዘ ይገኛል፡፡ ሺጂአንግ ግዛት ተገንጣይነትና የሽብር ድርጊት አንሰራርቷል በሚል ቻይና የደህንነት ስራውን አጠናክራለች፡፡ ቻይና 20 በመቶ የአለም የጥጥ ገበያ ፍላጎትን የምትሸፍን ሲሆን የበዛው ከዚሁ ግዛት የሚመጣ ስለመሆኑ መረጃዎች ያሣያሉ፡፡ በዚሁ ግዛት ሰራተኞች ላይ ከፍተኛ የጉልበት ብዝበዛ እንደሚፈፀም ሲገለፅ ቆይቷል፡፡ በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *