መደበኛ ያልሆነ

ጷግሜ 4፤2012-የብስራት ማለዳ አጫጭር መረጃዎች

~የቻድ መንግስት 12 ተነባቢ ጋዜጦች ህግን እያከበሩ አይደለም በሚል መዝጋቱ ተሰማ፡፡ ከተዘጉት ጋዜጦች መካከል አምስቱ በፈረንሳይኛ ቋንቋ የሚታተሙ ነበረ፡፡ የቻድ የሰብአዊ መብት ሊግ ድርጊቱን አሳፋሪ ብሎታል፡፡
~በአሜሪካ ያጋጠውን ሰደድ እሳት ተከትሎ አነስተኛ ከተሞች እንዲፈጠሩ ማድረጉ ተሰማ፡፡ በካሊፎርኒያ እና በሌሎች የአሜሪካ ምዕራባዊ ግዛቶች አነስተኛ ከተሞች በሰደድ እሳቱ ተበራክተዋል፡፡ በዋሽንግተን ግዛት ማሊኦን ከፍተኛ ውድመት አጋጥሟል፡፡
~ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ በዛሬው እለት በኢራቅ የሚገኘውን የአሜሪካ ወታደሮች ቁጥር እንደሚቀንሱ ይፋ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ አሜሪካ 5ሺ200 ወታደሮቿ በኢራቅ ይገኛሉ፡፡ በተመሳሳይ 8ሺ600 ወታደሮቿ በአፍጋኒስታን የሚገኙ ሲሆን ይህንን ቁጥር ወደ 4ሺ ዝቅ ለማድረግ ዋሽንግተን እቅድ አላት፡፡
~ፖፕ ፍራንሲስ ከኮሮና ቫይረስ በላይ ጎጂው ሃሜት ነው ሲሉ ተናገሩ፡፡ “ሃሜት የማህበረሰቡን ልብ የሚዘጋ ፣ አንድነትን የሚከፋፍል” ነው ብለዋል፡፡
~የቡድን ሰባት የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሮች ሩሲያዊው የመብት ተሟጋች አሌክሲ ናቫሊን መመረዙን ተከትሎ ድርጊቱን አወገዙ፡፡ የቡድን ሰባት አባል ሀገራቱ ከዚህ ጀርባ ያሉ በሙሉ ተጠያቂ ይሁኑ ብለዋል፡፡
~ለአለቃው የስድብ የፅሁፍ መልዕክት አስተላልፏል የተባለው የ 37ዓመቱ ፖኪስታናዊው አሲፍ ፐርቫቲ የሞት ፍርድ ተላለፈበት፡፡ ግለሰቡ የክርስትና እምነት ተከታይ ሲሆን በፓኪስታን በአናሳ ጎሳዎች ላይ ጠንካራ ህግ እየተተገበረ ነው ሲሉ የመብት ተሟጋቾች ይተቻሉ፡፡
~በህንድ ኬሬላ ከኮሮና ቫይረስ ነፃ የሚል ሰርተፍኬት ለመስጠት የአስገድዶ መድፈር ጥቃት የፈፀመው የጤና ኀላፊ በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡
በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *