መደበኛ ያልሆነ

ጷግሜ 5፤2012-ዶናልድ ትራምፕ ስለ ኮሮና ቫይረስ ገዳይነት ቢያውቁም ሆን ብለው ቀውሱን መሸሸጊያ አድርገዋል ሲል እውቁ ጋዜጠኛ በአዲሱ መጽሃፉ ይፋ ማድረጉ ተሰማ

ከወርሃ ታህሳስ እስከ ሀምሌ ድረስ ዶናልድ ትራምፕን ለ18 ጊዜ ቃለ መጠይቅ ያደረገላቸዉ ጋዜጠኛ ቦብ ዉድዋርድ እንደጻፈዉ ትራምፕ ስለ ኮሮና ገዳይነት ከጉንፋን በላይ ጎጂ መሆኑን አስቀድመዉ ያዉቁ የነበረ ሲሆን ነገር ግን ቀዉሱን ለማምለጫነት ሆን ብለዉ ተጠቅመዋል ሲል ለንባብ አብቅቷል፡፡

በዩናይትድ ስቴትስ ገና በኮሮና ቫይረስ ሞት መመዝገብ ሳይጀምር ትራምፕ ቫይረሱ ገዳይ ስለመሆኑ ከጋዜጠኛዉ ጋር በነበራቸዉ ቆይታ ተናግረዉ ነበር፡፡በአሜሪካ የሚገኙ የመገናኛ ብዙሃን በድጋሚ ቃለ መጠይቆቹን እያስተላለፉ ይገኛል፡፡

ይህ ጋዜጠኛ የጻፈዉ መጽሃፉ የፊታችን ማክሰኞ ለንባብ ይበቃል፡፡ጋዜጠኛዉ ቦብ ዉድዋርድ የዋተር ጌት ቅሌትን ይፋ ያደረገ ሲሆን በዚህም የተነሳ 37ኛዉ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሪቻርድ ኒክሰን ከስልጣናቸዉ እንዲወገዱ ያደረገ መረጃ እንደነበረም አይዘነጋም፡፡

ትራምፕ በአዲሱ የጋዜጠኛዉ መጽሃፉ መተቸታቸዉን ተከትሎ የፖለቲካ ስራ ቢሉትም የዲሞክራቱ ተቀናቃኛቸዉ ጆ ባይደን ፕሬዝዳንቱ ስራቸዉን መስራት አልቻሉም የዜጎችን ሞት አላስቀሩም ሲሉ ወቅሰዋቸዋል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *