መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 1፤2013-ከ19 ዓመታት በፊት ልክ በዛሬው እለት 19 የአልቃይዳ ታጣቂዎች አራት የመንገደኛ አውሮፕላኖችን በማገት የሽብር ጥቃት ተፈፀመ።

ንብረትነታቸው የአሜሪካና የዩናይትድ አየርመንገድ የሆኑት ሁለት አውሮፕላኖች የአለም የንግድ ማዕከል መንትያ ህንጻዎችን መቱ።

ባለ 110 ወለል ህንፃ ወደ ፍርስራሽነት ለመቀየር የወሰደበት ጊዜ 1 ሰዓት ከ42 ደቂቃዎች ብቻ ነበር።

ከሁለቱ ቀሪ አውሮፕላኖች አንዱ በፔንስላቫኒያ ሲከሰከስ ሌላኛው የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ዋና መስሪያ ቤት በፔንታጎን ተከስክሷል።

በታሪክ ከፍተኛ ደም አፍሳሽ የሚባለው ይህ ጥቃት ማክሰኞ ከጠዋቱ 8፡46 ጥፋቱ የጀመረበት ነበር።በጥቃቱ 2,977 ሰዎች ሲገደሉ ከ25ሺ በላይ ሰዎች የጉዳት ሰለባ ነበሩ።10 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር የሚያወጣ የንብረት ኪሳራ አጋጥሟል።

ጥቃቱ ከመድረሱ ከሁለት ቀናት በፊት በአለም የንግድ ማዕከል ውስጥ ህንፃውን ከጥቃት ለመጠበቅ የሚያስችል ስብሰባ የነበረ ቢሆንም ከተሰብሳቢዎቹ መካከል አንዳንዶቹ ስላልተመቻቸው እንዲዘዋወር ሆኗል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *