መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 4፣2013-የብስራት አመሻሽ አጫጭር ዓለም አቀፍ መረጃዎች

~ የጃፓን ገዢው ፓርቲ በዛሬው እለት የሺንዞ አቤን ምትክ ይመርጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ የሺንዞ አቤ የቅርብ አጋርና የመንግስት ካቢኔ ሃላፊ የ 71 ዓመቱ ዮሺሃይድ ሱጋ በዛሬው ምርጫ እንደሚያሸንፉ ይጠበቃል፡፡ ወግ አጥባቂው ኮንዘርቫቲቭ ሊበራል ዲሞክራቲክ ፓርቲ አዲሱን መሪ ዛሬ ከመረጡ በኋላ በህዝብ እንደራሴዎች በኩል ድጋሚ ምርጫ ይደረጋል፡፡ ከአርሶ አደር ቤተሰብ ቤት የተገኙት ሱጋ ከፍተኛ ተቀባይነት እያገኙ ይገኛል፡፡

~ ሳዑዲ አረቢያ ከስድስት ወራት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በነገው እለት ዓለም አቀፍ በረራን በከፊል እንደምታስጀምር አስታውቃለች፡፡ ከቫይረሱ ነፃ የሚልና ህጋዊ ሰነድ ያላቸው መንገደኞች ወደ ሳዑዲ መግባት ይችላሉ ተብሏል፡፡

~ ታሊባን በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ በፈፀመው የአየር ላይ ጥቃት 50 የሚጠጉ ሰዎች መገደላቸውን የአፍጋኒስታን የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

~ በአሜሪካ ምዕራባዊ ግዛት የተፈጠረው የሰደድ እሳት ተከትሎ የሟቾች ቁጥር 33 ደርሷል፡፡ በካሊፎርኒያ ፣ ኦሪገንና ዋሽንግተን ሰደድ እሳቱ ከፍተኛ ጥፋት አድርሷል፡፡

~ በሜክሲኮ የጋዜጠኞች ሞት አሳሳቢ ሁኖ ቀጥሏል፡፡ በአንድ ዓመት ውስጥ ብቻ 5 ጋዜጠኞች ተገድለው ተገኝተዋል፡፡ በ 2019 በሜክሲኮ 11 ጋዜጠኞች የተገደሉ ሲሆን በእርስ በእርስ ጦርነት ባለችው ሶሪያ ከተገደሉት 7 ጋዜጠኞች የበለጠ ነው፡፡ መረጃን ያጋልጣሉ በሚል ፍራቻ እንዲህ ዓይነቱ ድርጊት እየተወሰደ ይገኛል፡፡

~ በታንዛኒያ ከፍል ራስ ገዝ ግዛት በሆነችው ዛንዚባር በቀጣዩ ወር ለሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የምረጡኝ ቅስቀሳ ተጀመረ፡፡ በዛንዚባር ራስ ገዝ ጉዳይ ገዢው ፓርቲና ተቃዋሚዎች ውዝግብ ውስጥ ይገኛሉ፡፡

~ ታንዛኒያ እና ዩጋንዳ የድፍድፍ ነዳጅ ማስተላለፊያ ግንባታ የ 3.5 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ውል መፈራረማቸው ተሰማ፡፡ በውሉ መሰረት ግንባታው 1445 ኪ.ሜ ርዝማኔ እንዳለው ተሰምቷል፡፡ እ.ኤ.አ በ 2006 ዩጋንዳ የነዳጅ ክምችት ማግኘቷን ይፋ አድርጋ ነበር፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *