መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 5፤2013-ኢራን በደቡብ አፍሪካ የአሜሪካ አምባሳደር የሆነችውን ላና ማርክስን ለመግደል ስታሴር ነበረ መባሏን አስተባበለች፡፡

ኢራን በአሜሪካ በተገደለባት ጄነራል ቋሲም ሱሌይማኒ ምትክ የትራምፕ ወዳጅ ናት የምትባለዉን አምባሳደር ላና ማርክስን ለመግደል ስታሴር ነበር ብሎ ፖለቲኮ የዩናይትድ ስቴትስ ከፍተኛ ባለስልጣናትን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል፡፡

ሆኖም ኢራን በዉጪ ጉዳይ ቃል አቀባይ ሳኢድ ካሃቲብዛሂድ በኩል የአሜሪካ ዉንጀላ ያረጀ እና ዘመን ያለፈበት ስትል አጣጥላዋች፡፡ኢራናዊዉ የመካከለኛዉ ምስራቅ የሰላም አርክቴክት ይባል የነበረዉ ጄነራል ቋሲም ሱሌይማኒ በኢራቅ የባግዳድ አለም አቀፍ ኤርፖርት በአሜሪካ የሰዉ አልባ አዉሮፕላን ጥቃተ መገደሉ ይታወሳል፡፡

አምባሳደር ላና ማርክስን የዶናልድ ትራምፕ የቅርብ ሰዉ ስለመሆኗ ይነገራል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *