መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 5፤2013-ከቲያንስ ድርጅት ነን በማለት ከአንድ ሚሊየን ብር በላይ ያጭበረበሩ ሁለት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

በአዳማ ከተማ መስተዳድር ቦሌ ክፍለ ከተማ ጎሮ ቀበሌ እና ደካ አዲ ቀበሌ ውስጥ በተለያዩ ጊዜያት ፤ ከ80 ግለሰቦች ላይ አንድ ሚሊየን ሁለት መቶ ሺ ብር ያጭበረበሩ ሁለት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ግለሰቦቹን በአጭር ጊዜ ውስጥ እራሳቸውን መለወጥ እንደሚችሉ በማሳመን ከእያንዳንዳቸው 15 ሺ ብር እና ከዛ በላይ እንደተቀበሉ ተገልፆል፡፡

በዚህ የተታለሉት ግለሰቦቹም ከያሉበት ቦታ ሆነው ገንዘቡን አቅራቢያቸው በሚገኘው ኢትዮጰያ ንግድ ባንክ እንዳስገቡ ተገልፆል፡፡

ከቀናት በኋላ ጉዳዩ ግራ ያጋባቸው ተበዳዮች ለአዳማ ቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ በመሄድ መረጃ በመስጠታቸው ሁለት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራ እንደሆነ ብስራት ሰምቷል፡፡

በመሆኑም ህብረተሰቡ መሰል የማጭበር ወንጀሎች እንዳይገጥመው ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርበታል ሲሉ በአዳማ ከተማ መስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ ረዳት ኢንስፔክተር ወርቅነሽ ገልሜቻ ለብስራት ራዲዮ ዘጋቢዋ ሳምራዊት ስዩም ተናግረዋል፡፡

የንግድ ሚኒስቴር ቲያንስ የተባለውን ድርጅት ንግድ ፈቃድ ከአራት አመት በፊት ማገዱ ይታወሳል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *