መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 5፤2013-የብስራት ማለዳ አጫጭር ዓለም አቀፍ መረጃዎች

~ በአሜሪካ ተነባቢ የሆነዉ ታይም መጽሄት በሀገሪቱ በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸዉን ያጡ ሰዎች 200ሺ መቃረባቸዉን ተከትሎ የአሜሪካ ዉድቀት ሲል ሁኔታዉን ገልጾታል፡፡ኒዉ ዮርክ ታይምስ በበኩሉ በትክክለኛዉ አሃዝ መቀመጥ ቢችል የሟቾች ቁጥር ከ200ሺ ይልቃል ሲል ጽፏል፡፡አሜሪካ እንደ ልዕለ ሀያልነቷ የመሪነት ስፍራዋን መወጣት እንዳልቻለች በዘገባዎቹ ተካተዋል፡፡

~ የሩሲያዉ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን መንግስት ለቤላሩስ ፕሬዝዳንት ሉካሼንኮ አስተዳደር የ1.5 ቢሊየን ዩሮ ብድር እንዲሰጥ ይፋ አደረገ፡፡26 ዓመታት ቤላሩስን የመሩት ሉካሼንኮ ከስልጣን እንዲወርዱ ከፍተኛ ግፊት በህዝባቸዉ እየተደረገባቸዉ ይገኛል፡፡

~ ቻይና ለኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መከላከያ እያዘጋጀችዉ የምትገኘዉ ክትባት ከህዳር በፊት ዝግጁ እንደሚሆን ተነገረ፡፡ሶስተኛዉ ዙር የክትባቱ የክሊኒካል የሙከራ ሂደት እየተከናወነ ይገኛል፡፡

~ የእስያ የኢኮኖሚ እድገት ከ60 ዓመታት በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከፍተኛ ጉዳት እንዳጋጠመዉ ተነገረ፡፡የእስያ ልማት ባንክ እንዳስታወቀዉ በብሄራዊ ምርት እድገት ደረጃ የ0.7 በመቶ ቅናሽ ተመዝግቦበታል፡፡በቀጣይ 2021 ዓመት የኮሮና ቫይረስ መጥፋት ከቻለ ወደነበረበት ስፍራ ይመለሳል ሲል ባንኩ አስታዉቋል፡፡

~ በናይጄሪያ የሚገኙ የጤና ባለሙያዎች የተሻለ ክፍያ እና የስራ ስፍራ ያሻናል በሚል ለአንድ ሳምንት ይቆያል የተባለዉን የስራ ማቆም አድማ በትላንትናዉ እለት ጀምረዋል፡፡

~ የማይናማር ዋንኛ የተቃዋሚ ፓርቲ በወርሃ ህዳር የሚካሄደዉ ምርጫ በኮሮና የተነሳ እንዲራዘም ፍላጎት እንዳለዉ አስታወቀ፡፡

~ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በቻይና ዜጎች ጤናማ የምግብ ስርዓት እንዲከተሉ እያስገደደ መሆኑ ተሰማ።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *