መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 5፤2013-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ አዳዲስ ሹመቶች እና የስራ ምደባ ሰጥተዋል።


የተጀመረውን ለውጥ አጠናክሮ ለማስቀጠል እና በተለያዩ ግዜያት የሚነሱ የህዝብ ቅሬታዎችን ለመመለስ የአመራር ሽግሽግና አዳዲስ የስራ ስምሪት መስጠት አስፈላጊ በመሆኑ ለ8 አመራሮች ምደባ የሰጡት።
በዚሁ መሰረት ፦
1. አቶ ሙሉጌታ ተፈራ – የገቢዎች ቢሮ ኃላፊ
2. አቶ ተፈራ ሞላ – የሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ
3. አቶ ጀማል ረዲ – የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ
4. አቶ መኮንን አምባዬ – የቦሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ
5. አቶ ሺሰማ ገብረስላሴ- በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የከንቲባ የህዝብ አደረጃጀት አማካሪ
6. አቶ ተተካ በቀለ – በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የከንቲባ አደረጃጀት አማካሪ
7. አቶ ጥላሁን ፍቃዱ – በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የከንቲባ ማህበራዊ ጉዳዮች አማካሪ
8. አቶ የትናየት ሙሉጌታ – በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የህዝብ ቅሬታና አቤቱታ ማስተናገጃ ጽህፈት ቤት ኃላፊ
ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ተሿሚዎቹ የተሰጣቸው ሃላፊነት የህዝብ አገልጋይነት መሆኑን በመረዳት ህዝቡን በቅንነትና በታማኝነት ለማገልገል ዝግጁ እንዲሆኑ ማሳሰባቸውን የከተማ አስተዳደሩ ፕሬስ ሰክረተሪያት ጽህፈት ቤት ያወጣው መረጃ ያመለክታል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *