መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 5፤2013-የኢንሹራንስ ክፍያ ለማግኘት ከፍቅረኛዋ ጋር ተማክራ እጇን የቆረጠችዉ ግለሰብ በእስራት ተቀጣች

ዜግነቷ ከስሎቫኒያ የሆነችዉ የ22 ዓመቷ ጁሊጃ አዲሊሲክ ከሁለት አመት በፊት በአደጋ እጇ እንደተቆረጠ እና 1.2 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ካሳ እንዲከፈላት ለኢንሹራንስ ታመለክታለች፡፡የእርሷ እጅ በአደጋ እንደተቆረጠ በማስመሰል ገንዘቡን እንድታገኝ ወላጅ አባቷ እና ፍቅረኛዋ በሀሰተኛ ማስረጃ ተሳታፊ ሆኗል፡፡

ሆኖም ግን ለኢንሹራንስ እንዲሁም ለፖሊስ የተዛባ ቃል ስትሰጥ የነበረቸዉ ወጣቷ በስተመጨረሻ ከፍቅረኛዋ ጋር ተማክራ ሆን ብላ ግራ እጇ ስለመቁረጧ የእምነት ቃሏን ሰጥታለች፡፡

በዚህ የወንጀል ድርጊት የተነሳ ፍቅረኛዋ በሶስት ዓመት፣ጁሊጃ አዲሊሲክ በሁለት ዓመት እስር ሲቀጡ ሁኔታዉያን እያወቁ ያላጋለጡት አባት በአንድ ዓመት እግድ ተቀጥተዋል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *