መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 5፤2013-ዩ ቲዩብ በህንድ የቲክ ቶክ ተፎካካሪ የሚሆን መተግበሪያን ይፋ እንደሚያደርግ አስታወቀ

ንብረትነቱ የቻይና ከሆነዉ ቲክቶክ ጋር ተመሳሳይነት ያለዉ የዩ ቲዩብ ሾርትስ ተንቀሳቃሽ ምስል በ15 ሰከንድ ርዝማኔ ለማጋራት የሚያስችል አፕሊኬሽን መሆኑ ተሰምቷል፡፡

ህንድ ከቻይና ጋር በገባችበት የድንበር ዉዝግብ የተነሳ ቲክቶክን ጨምሮ 58 የቻይና መተግበሪያዎች /አፕሊኬሽኖች/ በሀገሯ እንዳይሰሩ አግዳለች፡፡

ለቻይና የቲክ ቶክ መተግበሪያ ዋንኛ መዳረሻ ህንድ የነበረች ሲሆን እገዳዉ እስከተላለፈበት ያሳለፍነዉ ሰኔ ድረስ በህንድ 120 ሚሊየን የቲክ ቶክ ተጠቃሚዎች ነበሩ፡፡የቲክ ቶክ መታገዱን ተከትሎ ክፍተቱን ለመሸፈን ዩ ቲዩብ ህንድን መዳረሻ አድርጓል፡፡

የዩ ቲዩብ የምርት አስተዳደር ምክትል ፕሬዝዳንት ክሪስ ጃፊ እንደተናገሩት ሾርትስ(YouTube Shorts) አጭር ፊልም ለመስራት፣ማራኪ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማጋራት የእጅ ስልክ በመጠቀም ብቻ የሚያግዝ መተግበሪያ ነዉ ብለዋል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *