መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 6፤2013-እስራኤል ዛሬ ማለዳ በጋዛ ሰርጥ የአየር ላይ ድብደባ ፈጸመች

እስራኤል ከአረብ ሀገራት ጋር የዲፕሎማሲ ግንኙነቷን ማሻሻሏን በመቃወም ፍልስጤማውያን አደባባይ ወጡ፡፡

በዌስት ባንክ እና በጋዛ ሰርጥ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰልፈኞች የተባበሩት አረብ ኤምሬትስና ባህሬን እስራኤልን ሀገር ናት ብለው መቀበላቸውን ከመቃወም ባለፈ የሮኬት ጥቃት ከፍልስጤም ወደ እስራኤል መፈፀሙ ተሰምቷል፡፡ በአፀፋ ዛሬ ማለዳ እስራኤል የአየር ላይ ድብደባን ፈፅማለች፡፡

በትናንትናው እለት በዋይት ሃውስ የእስራኤል ጠ/ሚ ቤንያሚን ኔታናሁ ከባህሬን እና ኤምሬትስ ባለስልጣናት ጋር የሰላም ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

በዌስት ባንክ ከተሞች ሄብሮን ፣ ናቡላስ እንዲሁም በጋዛ ራማላ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛን ያጠለቁ ሰልፈኞች ስምምነቱን አውግዘዋል፡፡

በዌስት ባንክ እና እየሩሳሌም ንብረትነቱ የእስራኤል የሆነ የግንባታ ተሸከርካሪ ቡልዶዘሮች የፍልስጤማውያኑን ቤት እያፈረሱ ነው ይህ ደግሞ በወገኖቻችን የአረብ ሃገራት በመከዳታችን ነው ብለዋል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *