መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 7፤2013-ኬንያ የዩጋንዳን ነዳጅ የማስተላለፍ እድል እንደሌላት ተንታኞች ተናገሩ

ዩጋንዳ እና ታንዛኒያ ለነዳጅ የማስተላለፊያ መስመር 3.5 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር የሚያወጣ ስምምነት መፈራረማቸዉን ተከትሎ ኬንያ ይህ እድል እንዳመለጣት ተንታኞች ተናግረዋል፡፡1,445 ኬ.ሜ ርዝማኔ ያለዉ የምስራቅ አፍሪካ የነዳጅ የማስተላለፊያ መስመር ከዩጋንዳ ሆማ እስከ ታንዛኒያ ታንጋ ድረስ የተዘረጋ ነዉ፡፡
በዩጋንዳ ታንዛኒያ የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ስፋቱ 61 ሴ.ሜ ስፋት ያለዉ ሲሆን በቀን እስከ 216ሺ ያልተጣራ ድፍድፍ ነዳጅ የማስተላለፍ አቅም ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ዩጋንዳ ለታንዛኒያ በበርሜል 12 ዶላር እንደምትከፍላት የሚጠበቅ ሲሆን ዩጋንዳ በቀን 2.6 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ገቢን ታገኛለች፡፡ታንዛኒያ በጥቅል ከታሪፍ 3.2 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር የምታገኝ ሲሆን ለ18 ሺ ሰዎች የስራ እድል ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ኬንያ የዩጋንዳን ነዳጅ የማስተላለፊያ እድሏ የጠበበ መሆኑን የአለም አቀፉ የስጋት ቁጥጥር አማካሪ ተቋም ይፋ አድርጓል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *