መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 7፤2013-የቬንዝዌላ መንግስት በሰብዓዊነት ላይ ወንጀል መፈጸሙን በምርመራ ስለማረጋገጡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ

የኒኮላስ ማዱሮ አስተዳደር የሰብዓዊ መብት ድንጋጌዎችን በመጋፋት ግድያና ሰዎችን ላይ አካላዊት ጉዳት ማድረሱን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አጣሪ ቢሮ በምርመራ ማረጋገጡን ይፋ አድርጓል፡፡የሀገሪቱ ተቃዋሚዎችን ዝም ለማሰኘት በፕሬዝዳንት ኒኮላስ ማዱሮ፣በመከላከያና የሀገር ዉስጥ ጉዳይ ሚንስትር የተመራ የወንጀል ተግባር መሆኑ በሪፖርቱ ተመላክቷል፡፡

ሪፖርቱን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሲያዘጋጅ ከ270 በላይ ሰዎችን ማነጋገሩን ያስታወቀ ሲሆን ተጎጂዎች፣የህግ ባለሙያዎች፣የአይን እማኞችና የቀድሞ ባለስልጣናት ተካተዉበታል፡፡ማዱሮ ያለ ፍርድ ቤት ዉሳኔ ዜጎች እንዲታሰሩ ስለማድረጋቸዉ በቂ ማስረጃ አግኝቻለዉ ሲል በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአጣሪ ተልዕኮ መሪ ፍራንሲስኮ ኮኤክስ ተናግረዋል፡፡

ከህግ ዉጪ በርካታ ጥሰት ፈጽሟል የሚባለዉን የማዱሮ አስተዳደርን ዋሽንግተን ለማሽመድመድ በርካታ ማዕቀቦችን መጣሏ ይታወቃል፡፡

በሚኪያስ ጸጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *