መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 8፤2013-በመላው ዓለም በኮሮና ቫይረስ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር ከ 30ሚሊዮን መብለጡን የጆን ሆፕ ኪንስ ዩኒቨርስቲ መረጃ ይፋ አደረገ

በ 2019 ማብቂያ በቻይና መቀስቀሱ የተነገረው የኮቪድ-19 የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እስከ ዛሬዋ ማለዳ ድረስ የ 950 ሺህ 555 ሰዎችን ህይወት ሲነጥቅ ከ 30 ሚሊዮን በላይ የቫይረሱ ተጠቂዎች ተመዝግበዋል፡፡

በቫይረስ ክፉኛ ከተጎዱ ሀገራት መካከል አሜሪካ ፣ ህንድና ብራዚል ቀዳሚውን ስፍራ ይዘዋል፡፡

በአሜሪካ ብቻ የተጠቂዎች ቁጥር 6.8 ሚሊዮን ሲደርስ 202ሺህ በላይ ሰዎች ህይወት ነጥቋል፡፡

የ 134ሺ ዜጎችን ህይወት በነጠቀባት ብራዚል በሟቾች ከአሜሪካ በመቀጠል ሁለተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡

የሁለቱ ሀገራት መሪዎች የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ደስተኛ ሆነዋል በሚል በበርካቶች ዘንድ ትችት የቀርብባቸዋል፡፡

በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *