መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 8፤2013-የብስራት ማለዳ አጫጭር መረጃዎች

~ የቀድሞዋ ሞዴል ኤሚ ዶሪስ እ.ኤ.አ በ 1997 በፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ በዩ.ኤስ.ኤ ኦፕን የሜዳ ቴኒስ ውድድር ወቅት ወሲባዊ ትንኮሳ እንደተፈፀመባት ጋርዲያን ቢዘግብም የትራምፕ የምርጫ ቅስቀሳ ዘገባውን አስተባብሏል፡፡ ጋርዲያን ለሰራው ዘገባ ተጠያቂ እንዲሆን እንሰራለን ሲል የትራምፕ የህግ አማካሪ ጄና አሊስ ተናግረዋል፡፡ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የብላክ ላይቭስ ማተር ተቀዋሚዎች ግራ ዘመም እና ፀረ አሜሪካ ናቸው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

~ በኒጀር ከተገደሉት ስድስት የፈረንሳይ ዜጎች የረድኤት ሰራተኞች ጥቃት ጋር በተያያዘ ፅንፈኛው እስላማዊ ቡድን አይኤስ/ዳኢሽ ሀላፊነቱን አንደሚወስድ አስታወቀ፡፡

~ ሞዛምቢክ በህገወጥ መንገድ የአሣ እርባታ የተነሳ በዓመት የ 60ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ኪሳራ እንዳጋጠማት አስታወቀች፡፡ በቀጣዩ ዓመት ከውጪ ሀገራት በጀልባ እየመጡ የአሳ ማስገር ስራን የሚሰሩ ሰዎችን ለመቆጣጠር በሳተላይት የታገዘ ስራ ሞዛምቢክ እንደምታስር አስታውቃለች፡፡

~ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የረድኤት ተቋም የሆነው የወርልድ ቪዥን ሰራተኞች ላይ በተሰነዘረ ጥቃት የጉዳት ሰለባ መሆናቸው ተሰማ፡፡ በኪቩ ግዛት ከወርልድ ቪዥን ሰራተኞች የአንዱ ሕይወት ማለፉን እና ሌሎች ክፉኛ መቁሰላቸውን ተሰምቷል፡፡

~ የቤላሩስ ፕሬዝደንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ በሀገሪቱ ውስጥ ለተፈጠረው ተቃውሞ ድጋፍ የሚያደርጉት የጎረቤት ሀገራት ናቸው ሲሉ ከፖላንድና ሉቲኒያ ጋር ቤላሩስን የሚያዋስኑ ድንበሮችን እንዲዘጋ ትዕዛዝ ሰጠ፡፡

~ የዩናይትድ ስቴትስ ባለስልጣናት ከ 40 ዓመታት በኋላ በታይዋን ጉብኝት ሊያደርጉ መሆኑን ተከትሎ በታይዋን አቅራቢያ ቻይና የጦር ልምምድ በዛሬው እለት ማድረግ ጀምራለች፡፡ ቻይና ታይዋንን እንደ እራሷ ግዛት ትቆጥራታለች፡:

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *