መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 11፤2013-በስፔን መዲና ማድሪድ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የወጡ መመሪያዎች አግላይ ናቸው ያሉ ዜጎች ለተቃውሞ አደባባይ መውጣታቸውን ተከትሎ በሀገሪቱ የኮሮና ቫይረስ በድጋሚ አገርሽቷል

በሀገሪቱ እንቅስቃሴን የሚከለክሉ መመሪያዎች ቢወጡም በገቢ ረገድ አነስተኛ የሆኑ አካባቢዎች ላይ የመመሪያው ጫና በርትቷል ያሉ የማድሪድ ነዋሪዎች ተቋማቸውን ገልፀዋል፡፡

ክልከላው ገቢን መሰረት ያደረገ ነው ያሉ ሰልፈኞች ‹‹ገቢያቸው አነስተኛ የሆኑ ሰዎችን መበደል ይቁም›› ሲሉ ድምፅ አሰምተዋል፡፡

በስፔን ከ 640ሺ በላይ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ሲገኙ ባለፉት ሁለት ሳምንታት ብቻ 120 ሺ የቫይረሱ ተጠቂዎች ተመዝግበዋል፡፡
30ሺ ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *