መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 11፤2013-የሆንግ ኮንግ ግዙፍ ባንክ (HSBC) በህገወጥ የገንዘብ ዝውውር እንዲካሄድ ማድረጉን አፈትልከው የወጡ መረጃዎች አረጋግጠዋል

ይህንኑ ጉዳይ በሚመለከት በፋይናንስ ወንጀል ግብረሃይል ኔትወርክ (FINCEN) በኩል የወጡ መረጃዎች አመልክተዋል፡፡

በአለም የሚገኙ ግዙፍ ባንኮች ወንጀለኞች 2 ትሪሊየን የአሜሪካን ዶላር የሚሆን ገንዘብ እንዲያዘዋውሩ ማድረጋቸው ተገልጿል፡፡

ይህ የፊንሴን መረጃ ከ 2500 በላይ ሰነድ ያለው ሲሆን የዓለም አቀፍ ባንኮች ሚስጥርን የዘረገፈ ሁኗል፡፡

በተለይ ከደንበኞቻቸው ጋር የነበረ የፋይናንስ ወንጀል ይፋ ተደርጓል፡፡

የሆንግ ኮንግ ባንክ ህገወጥ የሆነ ገንዘብን ስለማዘዋወሩ ፖፕ ሞርጋን የተባለው ኩባንያ በለንደን ባለው የባንክ አካውንት ከ 2 ቢሊየን በላይ የአሜሪካን ዶላር ያዘዋወረ ሲሆን ህጋዊ ሰነድ እንዳልነበረ ለማወቅ ተችሏል፡፡

የፕሬዝደንት ቫላድሚር ፑቲን የቅርብ ነው የሚባለው በለንደን የሚገኘው ባርክሌስ ባንክ በገንዘብ ዝውውሩ ተሳታፊ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡

በህገወጥ የገንዘብ ዝውውር ሚስጥራዊ ስራን ሲሰሩ ነበር የተባሉ ተቋማትን ገመና መረጃው እያጋለጠ ይገኛል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *