መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 11፤2013-የብስራት ማለዳ አጫጭር አለም ዓቀፍ መረጃዎች

~ የአሜሪካ ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዝዳንት ሩት ባደር ጊንስ በርግ ህልፈትን ተከትሎ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ በተያዘው ሳምንት ምትክ እጩ ለሴኔቱ እንደማያቀርቡ መናገራቸውን ጆ ባይደን ተቃወሙት፡፡ የትራምፕ አካሄድ የአሜሪካን ህግ የሚጣረስ ነው ሲሉ ባይደን ተናግረዋል፡፡

~ ሱዳን ከእስራኤል ጋር ያላትን የዲፕሎማሲ ግንኙነት ለማሻሻል ዝግጁ የሆነች ሲሆን በምላሹ 3 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ታገኛለች፡፡

~ በቤላሩስ መዲና ሚኒስክ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰልፈኞች የሀገሪቱ ፕሬዝደንት ስልጣን እንዲለቁ ከፍተኛ ተቃውሞ አድርገዋል፡፡ በተቃውሞ ፖሊስ ከሰልፈኞች ጋር መጋጨታቸው ተሰምቷል፡፡

~ የአይቮሪኮስት ፕሬዝዳንት ኦታሬ ለሶስተኛ ዙር ስልጣን እወዳደራለሁ ማለታቸውን የሀገሪቱ ተቃዋሚዎች እየተቹ ይገኛል፡፡ ተቃዋሚዎች ፕሬዝዳንቱ በድጋሚ በምርጫ እንዳይሳተፉ የሲቪል ተቋማት ጣልቃ አንዲገቡ ጠይቀዋል፡፡

~ በሜክሲኮ በኮሮና ቫይረስ የተነሳ ባለፉት 24 ሰዓት የ 235 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተሰማ፡፡ በመላው ሜክሲኮ በቫይረሱ ህይወታቸው ያጡ ሰዎች ቁጥር ከ 697ሺ ሲልቅ 73,493 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡

~ በኒውዝላድ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ክልከላ በመዲናዋ ኦክላንድ ከዛሬ ጀምሮ መነሳቱ ተሰማ፡፡ ሀገሪቱ የቫይረሱን ስርጭት በሚገባ መቆጣጠር ተነግሯል፡፡

~ ሆንድራስ በእስራኤል መዲና ቴላቪቭ የሚገኘውን ኤምባሲዋን 2020 ዓመት ሳይጠናቀቅ ወደ እየሩሳሌም እንደምታዞር አስታወቀች፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *