መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 11፤2013-የብስራት የምሳ ሰዓት ስፖርታዊ መረጃዎች

~ ጉንዶጋን በማንችስተር ሲቲ ቤት በኮቪድ-19 የተጠቃ ሶስተኛው ተጫዋች ሁኗል፡፡ ዛሬ ምሽት 3፡30 ዎልቭስን የሚገጥመው የፔፕ ጋርዲዮላ ቡድን ሶስት ቁልፍ ተጫዋቾቹን በኮሮና ቫይረስ የተነሳነው አጥቷል፡፡ ጀርመናዊው አማካኝ በኢትሀድ ስታዲየም ወረርሽኙ እንዳይሰራጭ አለም አቀፉ የጤና ተቋም /WHO/ ያስቀመጠውን መመሪያ ተግባራዊ ለማድረግ የሚገደድ ይሆናል፡፡ ሪያድ ማህሬዝ እንዲሁም አይመሪክ ላፖርፔ አስቀድመው በቫይረሱ መያዛቸው ይታወቃል፡፡

~ ማንችስተር ሲቲ በካሊዱ ኩሊባሊ ጉዳይ የተሰላቸ ይመስላል፡፡ አሁን ላይ የሲቪያው ተከላካይ ጁልስ ኩንዴ ላይ ትኩረቱን አድርጓል፡፡ ዎልቭሶች በ 30ሚሊዮን ፓውንድ ተከላካዩ ኔልሰን ሴሜዶን ከባርሴሎና ለማስፈረም ተቃርበዋል፡፡ ባሳለፍነው ወር ቶተንሀምን የተቀላቀለው ማት ዶኸርቲ ተተኪ ለማድረግ የ 26 ዓመቱን ፖርቹጋላዊ ማስፈረም ይሻሉ፡፡

~ ቶሪኖ በአርሰናሉ አማካይ ሉካስ ቶሬራ ላይ ያላቸው ፍላጎት መቀዛቀዙ ስካይ ስፖርት አስነብቧል፡፡ በ 22ሚሊዮን ፓውንድ ወደስፍራው ያቀናል ተብሎ የነበረ ቢሆን አሁን ላይ ፍላጎታቸው ተቀዛቅዟል፡፡ አሁን ላይ ቶማስ ፓርቲ ሊያጡ ይችላሉ ከተባሉት አትሌቲኮ ማድሪድ ጋር ስሙ በመያያዝ ላይ ይገኛል፡፡

~ ናታን አኬ ከማንችስተር ሲቲ ባላንጣ ጥያቄ ቀርቦለት እንደነበር ገለጸ፡፡ በ 40ሚሊዮን ፓውንድ ሲቲን የተቀላቀለው ተከላካዩ ከየትኛው ክለብ ጥያቄው እንደመጣ ግን መናገር አልፈለገም፡፡

~ አርሰናል የአይስላንዳዊውን ግብ ጠባቂ ሩናር አሌክስ ሩናርሰን በ 1ሚሊዮን ፓውንድ ዛሬ ይፈፅማል፡፡ ግብ ጠባቂው በለንድ የሚገኝ ሲሆን ለፈረንሳዩ ክለብ ዲጆን ተሰላፊ ነበር፡፡

~ በክሪስታል ፓላስ በሰፊ ጎል ሽንፈትን ያስተናገዱት ቀያዮቹ ሰይጣኖች ማንችስተር ዩናይትድ አሁንም የመሀል ተከላካይ ማስፈረም እንደማይፈልግ አሰልጣኙ ኦሊጎናር ሶልሻር ገለፀ፡፡

~ የ 28 ዓመቱ አማካይ አሌክስ ኦክስሌድ ቻምበርሊን እንደማይሸጥ ሊቨርፑሎች አስታወቁ፡፡

~ ናፖሊና ላዚዮ ሽኮርዳን ሙስታፊን ለማስፈረም ተፋጠዋል፡፡ አርሰናል ከተጫዋቹ ዝውውር ቢያንስ 13 ሚሊዮን ፓውንድ ይፈልጋል፡፡

~ ሊዮኔል ሜሲ ወደ ኢንተር ሚላን ላቀናው የቀድሞ የቡድን አጋሩ አንትሮ ቪዳል ይቅናህ ሲል በአጭር መልዕክት አበረታቶታል፡፡ የ 33ዓመቱ ኮከቡ ሁለት ዓመታት በባርሴሎና ማሳለፍ የቻለ ሲሆን በ 1ሚሊዮን ዩሮ ወደ ጣሊያኑ ክለብ ኢንተር አቅንቷል፡፡

በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *