መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 11፤2013-የተፀነሰውን ልጁን ፆታ ለማወቅ የሚስቱን ሆድ በመክፈት ጉዳት ያደረሰው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ

በህንድ ኡታር ፕራዴሽ ግዛት ነዋሪ የሆነው ፓንናላ የተባለው ግለሰብ ከባለቤቱ ጋር ለአመታት በፍቅር ሲኖር አምስት ሴት ልጆችን ማግኘት ችሏል።ሆኖም ወንድ ልጅ የመውለድ ፍላጎት ከፍተኛ ነበር።

ለስድስተኛ ጊዜ ባለቤቱ ነፍሰጡር መሆኗን ተከትሎ የፅንሱን ፆታ ለማወቅ የቸኮለው ባል የባለቤቱን ሆድ በስለት በመሰንጠቅ ለመመልከት መሞከሩ ለከፍተኛ የጤና ጉዳት አጋልጧታል።

ይህንኑ ተከትሎ ወደ ጤና ተቋም እንድታመራ ሲደረግ እርሱም በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *