መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 12፣2013-የብስራት ከሰዓት አጫጭር ስፖርታዊ መረጃዎች

 ቺሊያዊው አማካኝ አርትሮ ቪዳል በይፋ ኢንተር ሚላንን ተቀላቅሏል፡፡ ለክለቡ የፈረመ ስድስተኛው ቺሊያዊ ተጫዋች መሆን ችሏል፡፡
ለኤቨርተኑ
 ማንችስተር ዩናይትድ አጥቂ ካልቨርት ሌዊን ጥያቄ ያቀረበ ቢሆንም ፤ ተጫዋቹ ላይ የተለጠፈው 80ሚሊዮን ፓውንድ ከጨዋታው ውጪ ያደርጋቸዋል ተብሏል፡፡

 ማንችስተር ዩናይትድ ብራዚላዊውን የፖርቶ የግራ ተመላላሽ አሌክስ ቴሌስን ለማስፈረም የሚፈልጉ ሲሆን 23ሚሊዮን ፓውንድ ከተጫዋቹ ክለቡ ይፈልጋል፡፡ ዲያጎ ዳሎትን ገንዘብ ጨምሮ በልውውጥ ዩናይትድ በአማራጭ ቢያቀርብም ተቀባይ አልሆነም፡፡

 አርሰናል ቶማስ ፓርቲን ወደ ክለቡ ለማምጣትና ሉካስ ቶሬራን በአማራጭ ለማቅረብ ተዘጋጅተዋል፡፡ ክለቡ ጋናዊውን የአትሌቲኮው ማድሪድ አማካይ ለማስፈረም ክረምቱን ሙሉ ጥረት ሲያደርግ መቆየቱ ይታወቃል፡፡ ይሁንና አትሌቲኮ የጠየቀውን 45ሚሊዮን ፓውንድ ማቅረብ አልቻለም፡፡

 የባርሴሎና ክዋክብት የቀድሞ ወኪል ፋብያን ሶልዲኒ በ 2003 ከአርሰናል ከፍተኛ ፍላጎት መታየቱን ተከትሎ ሊዮኔል ሜሲ እንደ ፋብሪጋዝን ወደ አርሰናል ሊያቀና ተቃርቦ እንደነበር ተናገረ፡፡

 የ 24ዓመቱ የቀድሞው የሊቨርፑል ተጫዋች ጆርዳን ኢቤ ለደርቢ ካውንቲ በሁለት ዓመት ውል ፈርሟል፡፡

 የማጎየር አጣማሪን ማስፈረም የግድ ያስፈልጋል ሲሉ የማንችስተር ዩናይትድ የቀድሞ አሰልጣኝ አሌክስ ፈርጉሰን ረዳት የነበሩት ማክ ክላረን ለአሰልጣኙ ኦሊ ምክር ሰጥተዋል፡፡ ለቀያዮቹ ሰይጣኖች ቪክቶር ሊንዶሎፍን መተካት የግድ ነው ብለዋል፡፡

 በሞሪንሆ እምነት ያጣው አሊ ስሙ ከፒኤስጂ ጋር በመያያዝ ላይ ሲሆን ከኔይማር እና ምባፔ ጋር ሁነኛ ጥምረት ይፈጥራል እየተባለ ይገኛል፡፡

 ሉዊስ ስዋሬዝ ከአትሌቲኮ ማድሪድ ጋር ስምምነት ላይ ቢደርስም የባርሴሎና ቦርድ ዝውውሩ እንዲጓተት እያደረጉት ስለመሆኑ ተደምጧል፡፡ ተጫዋቹ አስቀድሞ ስሙ በስፋት ከጁቬንትስ ጋር መያያዙ አይዘነጋም፡፡

በሚኪያስ ጸጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *