መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 12፤2013-በአሜሪካ ስርዓት አልበኝነት(አናርኪዝም) ገኖባቸዋል ከተባሉ ሶስት ከተሞች መካከል ኒውዮርክ እንዳለችበት ዋይት ሀውስ አስታወቀ


የትራምፕ አስተዳደር እንዳስታወቀው ስርዓት አልበኝነት ተስፋፍቶባቸዋል የተባሉ ሶስት ከተሞች መለየታቸዉን ተከትሎ ከፌደራል መንግስት የሚያገኙት ድጋፍ እንደሚቀንስ ይፋ አድርጓል፡፡
ስርዓት አልበኝነት ነግሶባቸዋል የተባሉት ሶስት ከተሞች ኒዉዮርክ፣ፖርትላንድና ሲያትል መሆናቸዉን ዋይት ሀዉስ አስታዉቋል፡፡የከተሞቹ ከንቲባዎች በበኩላቸዉ ችግሩን ለመፍታት ቃል በመግባት የትራምፕ አስተዳደር ፖለቲካዊ አቋም እንደያዘ ግን ነቅፈዋል፡፡
የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ አቃቢ ህግ ዊሊያም ባራ የፌደራሉ በጀት ብክነት ላይ እንዳይዉል ያግዛል የከተሞቹ አስተዳደሮች የዜጎችን ደህንነት የማስጠበቅ ስራ መስራት መጀመር አለባቸዉ ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በሶስቱ ከተሞች የጦር መሳሪያ ያልታጠቀዉ ጥቁሩ አሜሪካዊ ጆርጅ ፍሎይድ መገደሉን ተከትሎ ከፍተኛ ተቃዎሞ ሲደረግባቸዉ መሰንበቱ ይታወሳል፡፡ግጭት ወለድ ወንጀሎች ከ1990ዎቹ ወዲህ በአሜሪካ የመቀነስ አዝማሚያ አሳይቶ የነበረ ቢሆንም አሁን ላይ በድጋሚ እያገረሸ ስለመሆኑ መረጃዎች አመላክተዋል፡፡

በሚኪያስ ጸጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *