መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 12፤2013-በአፍጋኒስታን መንግስትና የታሊባን ታጣቂዎች መካከል ከባድ የተባለ ዉጊያ ተካሄደ

ሁለቱ ከአካለት በኳታር መዲና ዶሃ የሰላም ስምምነት ንግግር ከጀመሩ በኃላ የተካሄደ ዉጊያ መሆኑን ምንጮች ጠቁመዋል፡፡በሀለቱ አካላት መካከል ባሳለፍነዉ እሁድ ምሽት ከፍተኛ ዉጊያ በአፍጋን የተለያዩ ግዛቶት ተካሂዷል፡፡

ዉጊያ ከነበረባቸዉ ግዛቶች መካከል ሂልማንድ፣ካፒሳ፣ባግሃላን፣ኩንዱዙና ባላክ ተጠቃሽ ናቸዉ፡፡በነበረዉ ከባድ ዉጊያ 57 የአፍጋን የደህንነት ሀይሎች ሲገደሉ በአጸፋዉ በተወሰደዉ እርምጃ 80 የታሊባን ታጣቂዎች ተገድለዋል፡፡

በየእለቱ በዶሃ ሁለቱ አካላት ሰላም ለማዉረድ ሲያደርጉበት የነበረዉ ድርድር የመሳካቱ ሁኔታ ጥያቄ ዉስጥ ገብቷል፡፡ታሊባን የአሻራፍ ጋኒን አስተዳደር ከስልጣን በማስወገድ በአሜሪካ ክንድ ከተባረረበት የካቡል ቤተመንግስት ለመመለስ ከፍተኛ ትግሉን ቀጥሏል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *