መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 13፤2013-በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጉባኤ ላይ የተደመጡ አይረሴ የመሪዎች ንግግር

~ ሙሃመር ጋዳፊ ፡- ይህንን የፀጥታው ምክር ቤት የምትሉትን የሽብር ምክር ቤት ብላችሁ ብትጠሩት ይሻላል፡፡ (ንግግራቸው 100 ደቂቃ ርዝማኔ ነበረው)

~ የቀድሞ የኢራን መሪ አህመዲን ጃድ ፡- የአሜሪካውያን እና አውሮፓውያን መብትና ክብር ጥቂት በሆኑት ፂሆናውያን እጅ ላይ ጨዋታ ሆኗል ብለዋል፡፡

~ የቀድሞ የቬንዙዌላ ፕሬዝዳንት ሁጎ ቻቬዝ ፡- ‹‹ትናንትና አጋንንቱ እዚህ ነበር አሁን ድረስ ይህ ቦታ ሰልፈር ሰልፈር ይሸታል›› ሲሉ አማትበዋል፡፡ ሴጣን ሲሉ የገለጿቸው የቀድሞውን የአሜሪካን ፕሬዝደንት ጆርጅ ቡሽን ነበር፡፡

~ ፊደል ካስትሮ፡- ኬኒዲ ወይ ሚሊየነር አልሆንክ አልያም አልተማርክ ሲሉ ተናግረዋቸዋል፡፡ አራት ሰዓት ከ 30ደቂቃ ነበር መልዕክት ያስተላለፉት።

©ስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *