መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 13፤2013-በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዓመታዊ ጉባኤ ላይ የቻይና አሜሪካ ውዝግብ ቀጥሏል

በኒውዮርክ በቨርቹዋል አማካኝነት እየተካሄደ የሚገኘው ጉባኤ ላይ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ለኮሮና ቫይረስ መዛመት ቻይናን በመወንጀል ተጠያቂ ልትሆን ይገባል ብለዋል፡፡

የቻይና ፕሬዝደንት ሺ ጂንፒንግ በበኩላቸው ቤጂንግን ከየትኛውም ሀገር ጋር ወደ ቀዝቃዛው ጦርነት መግባት አትፈልግም ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ሁለቱ ሀገራት በተለያዩ ጉዳዮች ውዝግባቸው እያየለ ይገኛል፡፡ የዘንድሮ የመንግስታቱ ድርጅት ጉባኤ ገፅ ለገፅ አለመሆኑን ተከትሎ በጆኦፖለቲካ ውጥረት ውስጥ ያሉ ሀገራት የሚያሳዩት አካላዊ ብሽሽቅን አስቀርቷል፡፡

ትራምፕ በንግግራቸው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በቻይና ሲቀሰቀስ የሀገር ውስጥ በረራን ክልከላ ዓለም አቀፍ በረራ ግን እንዲደረግ ስታደርግ ነበረ ሲሉ ወቅሰዋል፡፡

ሺ ጂፒንግ በበኩላቸው ልዩነትን ለማጥበብ መስራታችንን እንቀጥላለን ሲሉ ፀብ ጫሪ ንግግሮች የዜሮ ድምር ጨዋታ ነው ሲሉ ጠርተውታል፡፡

በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *