መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 18፤2013-አርሜንያ እና አዘርባጃን በድንበር ግጭት ውስጥ መግባታቸው ተሰማ

በአለማችን እድሜ ካስቆጠሩ ግጭቶች መካከል በአዘርባጃን እና አርሜንያ የድንበር ይገባኛል ግጭት አንዱ ነው፡፡

በቀድሞ የሶቬት ህብረት ውስጥ የነበሩት ሀገራቱ በናጎራኖ እና ካራባክ ግዛቶች በትላንትናው እለት ግጭት ውስጥ መግባታቸውን ተከትሎ ቢያንስ የ 23ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡

የዓለም አቀፍ መንግስታት ለአዘርባጃን በወሰነው ግዛት ውስጥ የአርሜንያ ዜጎች ተቆጣጥረውት ይገኛል፡፡

የአዘርባጃን ፕሬዝዳንት አሊየቪ ግዛቱን በድጋሚ እንቆጣጠራለን ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በሁለቱ ሀገራት የድንበር አካባቢዎች ያገረሸውን ግጭት ተከትሎ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቀጥሏል፡፡

ሀገራቱ የሚወዛገቡበት ስፍራ ኦካስፒን ባህር የተፈጥሮ ጋዝና ነዳጅ የሚተላለፍበትን መስመር በቁጥጥራቸው ስር ለማዋል ነው፡፡

ስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *