መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 18፤2013-የብስራት ማለዳ አጫጭር ዓለም አቀፍ መረጃዎች

~ ስሪላንካ ከእንግሊዝ በቆሻሻ የተሞላ ኮንቴይነርን ቢላክላትም መልሳ ወደ እንግሊዝ መላኳ ተሰማ፡፡ በ21 ኮንቴነር 260ሺ ኪ.ግ የሚመዝን ቆሻሻ ከእንግሊዝ የተላከላት ስሪላንካ ድርጊቱን የዓለም አቀፉ ማህበረሰብን ህግ የሚጣረስ ብላዋለች፡፡

~ በቤላሩስ ሚኒስክ ከተማ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰልፈኞች የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ ከስልጣን እንዲለቁ ተቃውሞ ማድረጋቸው ተሰማ፡፡ ይህንኑ ተከትሎ ፖሊስ ቢያንስ 200 ሰልፈኞች በቁጥጥር ስር አውሏል፡፡

~ በህንድ በኮሮና ቫይረስ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር ከስድስት ሚሊዮን መብለጡ ተሰማ፡፡ ባለፉት 24ሰዓት 1039 ሰዎች በቫይረሱ ሕይወታቸውን ማጣታቸውን ተከትሎ በህንድ በኮሮና ቫይረስ የሟቾች ቁጥር 95542 ደርሷል፡፡

~ ኢራን እና ኢራቅ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ለማሳደግ መስማማታቸው ተሰማ፡፡ ሀገራቱ በቀጠናው ያለውን የዩናይትድ ስቴትስ ሚና ምን መሆን አለበት በሚለው ዙሪያ መክረዋል፡፡

~ በግብፅ ፕሬዝደንት አብዱልፈታህ አልሲሲ ላይ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ፕሬዝዳንቱ አለመረጋጋት በፈጠሩ ተቃዋሚዎች ላይ ቁጣቸውን ገልፀዋል፡፡

~ የቀድሞ የማሊ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሞክታር ኦዩኤኒ ጊዜያዊ የሀገሪቱ የሽግግር ጠ/ሚ ተብለው ተሾሙ፡፡ ሹመቱ የማሊ ጎረቤቶች በሀገሪቱ ላይ የተጣለው ማዕቀብ እንዲነሳ ያግዛል ተብሏል፡፡

~ የኳታር ዓየር መንገድ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የተነሳ ያጋጠመውን ኪሳራ ለመደገፍ የኳታር መንግስት ሁለት ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር እርዳታን ለአየር መንገዱ እንደሚያደርግ አስታወቀ፡፡

ስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *