መደበኛ ያልሆነ

ዛሬ መስከረም 19፤2013-በአምስት ቀናት ውስጥ ብቻ አራት ጊዜ የግድያ ሙከራ ተደርጎባቸው የተረፉት ፕሬዝዳንት ኮ/ል መንግስቱ ሃ/ማርያም!!

ኮ/ል መንግስቱ ሃ/ማርያም ወደ ስልጣን ላይ በወጡ በሁለተኛው አመት ማለትም መስከረም ወር 1969 ዓ/ም በእርሳቸው ላይ ለአራት ያክል ጊዜ የሞት ድግስ ተደግሶላቸው ከእዛ ድግስ መትረፍ እንደቻሉ ፀሃፍት ይነግሩናል፡፡

ነገሩን አስገራሚ የሚያደርገው በፕሬዝዳንቱ ላይ ከመስከረም 8 ቀን 1969 እስከ መስከረም 13 ቀን ባሉት ተከታታይ ስድስት ቀናት ውስጥ ብቻ ለ4 ጊዜ ከተደገላቸው የሞት ድግስ ውስጥ አራተኛው ማለትም መስከረም 13 ቀን 1969 ዓ.ም ላይ የተሞከረው የግድያ ሙከራ ታፋቸውን በጥይት ተመተው እንዲቆስሉ አደረጋቸው፡፡

ጠባቂያቸው አለቃው እላያቸው ላይ በመደረብ በፕሬዝዳንቱ ላይ ሊያርፍ የነበረው ሁለተኛ የጥይት ቀልሃ በገዛ አካሉ ተቀብሎ መሪያውን አዳነ፡፡

ከእዚህ የግድያ ሙከራ አስቀድሞ የመጀመሪያው የግድያ ሙከራ መስከረም 8 1969 የተሞከረው ሲሆን ፕሬዝዳንቱ መምጣታቸውን የመብራት ምልክት እንዲሰጥ የተመደበው ቴዎድሮስ መብራቱ ተከተል የተባለው ሰው የተሳሳተ ምልክት በመስጠቱ ሳይሳከ ቀረ፡፡

ሁለተኛው ሙከራ በማግስቱ መስከረም 9 1969ዓ.ም የተደረገባቸው ሲሆን በእዚህ ጊዜ ፕሬዝዳንቱ ግድያውን እንዲፈፅሙ የተመረጡት ወታደሮች ለሌላ ግዳጅ ተልከው በመሄዳቸው ሳይሆን ቀረ።

ከእነዚህ ሶስት ያልተሳኩ የግድያ ሙከራዎች በኋላ አራተኛዋ እና መስከረም 13 ቀን 1969 ዓ.ም ምሽት ላይ ከስራ ወደ መኖሪያ ቤታቸው እያመሩ ግዮን ሆቴል ፊት ለፊት በኢህአፓ ታጣቂዎች የወረደባቸው የጥይት እሩምታ ታፋቸውን ካቆሰለው በኋላ ሁለተኛው ጥይት እርሳቸው ላይ እንዳያርፍ ከለላ በሆናቸው ጠባቂያቸው አማካይነት ህይወታቸው ሊተርፍ ችሏል፡፡

ናትናኤል ሀብታሙ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *