መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 22፤2013-የብስራት ማለዳ አጫጭር ዓለም አቀፍ መረጃዎች

~ በአዘርባጃንና አርሜንያ መካከል የተነሳው ውጊያ አምስተኛ ቀኑን ያስቆጠረ ሲሆን ሁለቱ አካላት የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ እንዲደርሱ የቀረበላቸዉን ጥሪ ውድቅ አድርገዋል፡፡

~ የብራዚል ግዙፍ ከተማ የሆነችው ሳኦ ፖሎ ትምህርት ቤቶችን በድጋሚ ለመክፈት እንዲቻል የኮሮና ቫይረስ የዘመቻ ምርመራ ማስጀመሯ ተሰማ፡፡በብራዚል በወረርሽኙ የተነሳ የ144,767 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡

~ በሰሜናዊ ናይጄሪያ ባጋጠመ የጎርፍ አደጋ 41 ሰዎች ህይወታቸውን ሲያጡ ከ100ሺ በላይ ሰዎች ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸው ተሰማ፡፡

~ በኢራቅ መዲና ባግዳድና በሌሎች ከተሞች የሚገኙ ሰልፈኞች አደባባይ በመውጣት በሀገሪቱ የማሻሻያ ጥያቄ የተነሳበት አንደኛ ዓመት ተዘክሯል፡፡

~ የሰሜን ኮርያ መሪ ኪም ጆን አን እና እህታቸዉ በሀገሪቱ በጎርፍ አደጋ የተጎዱ ስፍራዎችን ጎበኙ፡፡ክፉኛ ከወር በፊት በጎርፍ የተጎዳው አካባቢ በድጋሚ ማገገሙ ተከትሎ ኪም አድናቆታቸውን ቸረውታል፡፡

~ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የነጭ የበላይነትን የሚያቀነቅኑ ቡድኖችን አወገዙ፡፡ፕሬዝዳንቱ ከጆ ባይደን ጋር በነበራቸዉ ቆይታ ይህንን ሀሳብ ላይ ዝምታ መምረጣቸዉ ሲያስቅሳቸዉ ነበር፡፡

~ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ዙርያ የተዛባ መረጃ በመስጠት ዋንኛ ግለሰብ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ናቸዉ ሲል በኒዉዮርክ ዋና መቀመጫዉን ያደረገዉ የጥናትና ምርምር ተቋም የሆነው ኮርኔል ዩኒቨርሲቲ ይፋ አድርጓል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *