መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 29፤2013-አሜሪካ በኢራን ላይ ተጨማሪ ማዕቀብ ጣለች

በትላንትናዉ እለት የዋሽንግተን አስተዳደር እንዳስታወቀዉ በኢራን የፋይናንስ ሴክተር ላይ በተለይም በ18 ባንኮች ላይ ማዕቀብ ተጥሏል፡፡ከእነዚህ የፋይናንስ ተቋማት ጋር የሚሰሩ በአሜሪካ የሚገኝ ሀብት በሙሉ እንዳይንቀሳቀስ ማዕቀብ ተጥሏል፡፡

ማዕቀቡ የግብርና ምርቶችን፣የመድሃኒት፣የምግብና የህክምና ቁሳቁስ ግዢን የሚመለከት አይደለም፡፡የኢራን የዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ሞሃመድ ጃቫድ ዛሪፍ የአሜሪካን ዉሳኔ በመተቸት በኮሮና ወረርሽኝ ወቅት ኢራንን ዋጋ ለማስከፈል የታለመበት ሲሉ ኮንነዋል፡፡

የኢራን ማዕከላዊ ባንክ ገዢ ሂማቲ የማዕቀብ ዉሳኔዉ የፖለቲካ ፕሮፖጋንዳ ነዉ ሲሉ ወቅሰዋል፡፡በኢራንና አሜሪካ መካከል በ2015 ከተደረሰበት የኒዉክሌር መርሃ ግብር ስምምነት በ2018 የትራምፕ አስተዳደር በማፈግፈጉ ሀገራቱን ለዉዝግብ ዳርጓል፡፡

ሚኪያስ ጸጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *