መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 29፤2013-የ2020 የኖቤል የሰላም አሸናፊ የአለም የምግብ ፕሮግራም(WFP) ሆነ

የኖርዌይ የኖቤል ሽልማት ኮሚቴ እንዳስታወቀው የዓለም የምግብ መርሃ ግብሩ ረሃብን ለመዋጋት ያደረገው ጥረት ተሸላሚ አድርጎታል ብሏል።101ኛ የኖቤል የሰላም አሸናፊው WFP 10 ሚሊየን የስዊዲን ክሮን ወይንም 1.1 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ይቀበላል።

የዓለም የምግብ ፕሮግራም ዋና ሀላፊ ዴቪድ ቢአስሊ ለመጀመሪያ ጊዜ በህይወቴ ቃላቶች አጠሩኝ ሲሉ ለአሶሴትድ ፕሬስ ተናግረዋል።

ለሽልማቱ 211 ግለሰቦች እና 107 ተቋማት ታጭተው ነበር።የአለም የጤና ድርጅትና የአየር ንብረት ለውጥ ተሟጋቿ ግሪታ ተንበርግ ለአሸናፊነት ግምት ተሰጥቷቸው ነበር።

በስውዲናዊው ስራ ፈጣሪ አልፍሬድ ኖቤል ስም ሽልማቱ እ.ኤ.አ በ1901 መሰጠት ተጀምሯል።ጠ/ሚ አብይ አህመድ ያለፈው ዓመት ተሸላሚ እንደነበሩ ይታወሳል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *