መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 29፤2013-ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከነገ ጀምሮ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴ እንደሚመለሱ የግል ሀኪማቸው አስታወቁ


በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መጠቃታቸው ከሳምንት በፊት ይፋ የተደረገዉ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የጤናቸዉ ሁኔታ መሻሻልን ማሳየቱን ዶ/ር ሲአን ኮንሌ ተናግረዋል፡፡ትራምፕ በቫይረሱ ከተጠቁ ከአስር ቀናት በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴ በነገዉ እለት ይጀምራሉ፡፡
የአሜሪካ የበሽታ መቆጣጠርና መከላከል ማዕከል(ሲዲሲ) አንድ በኮሮና ቫይረስ የተጠቃ ሰዉ በአስር ቀናት ዉስጥ ከሚያሳየዉ ምልክት የጤናዉ ሁኔታ ስለመሻሻሉ ጠቋሚ ሊሆን እንደሚችል መመሪያ አስቀምጧል፡፡
ትራምፕ በኮሮና ቫይረስ መጠቃታቸዉን ተከትሎ ከአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ጋር የተያያዙ በርካታ መርሃ ግብሮችን ሰርዘዋል፡፡ምናልባትም በድጋሚ የምረጡ ቅስቀሳቸዉን ነገ ምሽት በፍሎሪዳ እንደሚጀምሩ ይጠበቃል፡፡
አስቀድሞ ግን በዛሬዉ እለት ከኮቪድ ነጻ ስለመሆናቸዉ ምርመራ ይደረግላቸዋል፡፡


በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *